የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 114
  • “ሰባት ቀሳፊ ኃጢአቶች” አሉ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ሰባት ቀሳፊ ኃጢአቶች” አሉ?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • ኃጢአት ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ‘ይቅር ለማለት ዝግጁ’ የሆነ አምላክ
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
  • አምላክ ኃጢአታችንን እንድንናዘዝ ይጠብቅብናል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • የኃጢአት ትርጉሙ ጠፍቶብን ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 114
ያዘነ ሰው

“ሰባት ቀሳፊ ኃጢአቶች” አሉ?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ “ሰባት ቀሳፊ ኃጢአቶች” ተብለው የተሰየሙ የኃጢአት ድርጊቶችን ለይቶ አይጠቅስም። ሆኖም አንድ ሰው ከባድ ኃጢአቶችን የሚፈጽም ከሆነ መዳን እንደማያገኝ ያስተምራል። ለምሳሌ ያህል፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ፆታ ብልግና፣ ጣዖት አምልኮ፣ መናፍስታዊ ድርጊት፣ በቁጣ መገንፈል እንዲሁም ስካር የመሳሰሉትን ከባድ ኃጢአቶች “የሥጋ ሥራዎች” በማለት ይጠራቸዋል። ከዚያም በመቀጠል እንዲህ ይላል፦ “እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽሙ የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።”—ገላትያ 5:19-21a

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ‘የሚጸየፋቸውን ሰባት ነገሮች’ ይዘረዝራል?

አዎ፣ ይዘረዝራል። ምሳሌ 6:16 እንዲህ ይላል፦ “ይሖዋ የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም እሱ የሚጸየፋቸው ነገሮች ሰባት ናቸው።” ሆኖም በምሳሌ 6:17-19 ላይ የሚገኘው የኃጢአቶች ዝርዝር ሁሉንም ኃጢአቶች ያካተተ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ከአስተሳሰብ፣ ከንግግር እንዲሁም ከድርጊት ጋር የተያያዙትን ጨምሮ ሁሉንም ዓይነት ኃጢአቶች የሚወክሉ ክፍሎችን የያዘ ነው።b

“ቀሳፊ ኃጢአት” የሚለው አገላለጽ ምን ያመለክታል?

አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች 1 ዮሐንስ 5:16 ላይ ይህንን አገላለጽ ተጠቅመውበታል። ለምሳሌ ያህል፣ ዘ ኒው አሜሪካን ባይብል “ቀሳፊ ኃጢአት አለ” ይላል። እዚህ ጥቅስ ላይ “ቀሳፊ ኃጢአት” ተብሎ የተተረጎመው አገላለጽ “ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። ታዲያ “ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት” እና “ለሞት የማያበቃ ኃጢአት” ልዩነታቸው ምንድን ነው?—1 ዮሐንስ 5:16

መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም ዓይነት ኃጢአት ሞት እንደሚያስከትል በግልጽ ይናገራል። ሆኖም በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት ከኃጢአትና ከሞት መዳን እንችላለን። (ሮም 5:12፤ 6:23) በመሆኑም “ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት” የሚባለው የክርስቶስ ቤዛ ምሕረት የማያስገኝለት ዓይነት ኃጢአት ነው። እንዲህ ዓይነቱን ኃጢአት የሚፈጽም ሰው፣ ሆነ ብሎ የኃጢአት ጎዳና የሚከተል ሲሆን አመለካከቱንም ሆነ ድርጊቱን ለመቀየር ፈቃደኛ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ዓይነቱን ኃጢአት ‘ይቅር የማይባል ኃጢአት’ በማለትም ይጠራዋል።—ማቴዎስ 12:31፤ ሉቃስ 12:10

የሰባቱ ቀሳፊ ኃጢአቶች ዝርዝር የመጣው ከየት ነው?

‘ሰባቱ ቀሳፊ ኃጢአቶች’ የተመሠረቱት ስምንት ዋና ዋና መጥፎ ድርጊቶች በተጠቀሱበት ዝርዝር ላይ ነው። ይህን ዝርዝር በአራተኛው መቶ ዘመን ያዘጋጀው ኢቫግሪየስ ፖንቲከስ የተባለ የሕዝበ ክርስትና መነኩሴ ነው፤ የዚህ ሰው ሥራ ጆን ካሸን ለተባለው መነኩሴና ባሕታዊ ሥራዎች መነሻ ሆኗል። በስድስተኛው መቶ ዘመን ቀዳማዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ግሪጎሪ፣ ካሸን ያዘጋጀውን የስምንት መጥፎ ድርጊቶች ዝርዝር ወደ ሰባቱ ቀሳፊ ወይም ዋና ዋና ኃጢአቶች ዝርዝር ቀየሩት፤ በሮም ካቶሊክ ሃይማኖታዊ ትምህርት መሠረት እነዚህ ኃጢአቶች ኩራት፣ ስግብግብነት፣ ፍትወት፣ ቅናት፣ ሆዳምነት፣ ቁጣ እና ስንፍና ናቸው። ግሪጎሪ እነዚህን ኃጢአቶች፣ የሌሎች ኃጢአቶች መነሻ የሆኑ ዋና ወይም አቢይ ኃጢአቶች አድርገው ተመልክተዋቸዋል።

a በገላትያ 5:19-21 ላይ የሚገኘው የ15 ከባድ ኃጢአቶች ዝርዝር ሁሉንም ኃጢአቶች አካትቶ የያዘ አይደለም፤ ምክንያቱም ጥቅሱ እነዚህን ኃጢአቶች ከዘረዘረ በኋላ “እነዚህን የመሳሰሉ” ይላል። ስለሆነም አንባቢው የማስተዋል ችሎታውን ተጠቅሞ እዚህ ዝርዝር ውስጥ ያልተካተቱ ሆኖም“እነዚህን የመሳሰሉ” ሊባሉ የሚችሉ ነገሮች የትኞቹ እንደሆኑ መረዳት ይጠበቅበታል።

b ምሳሌ 6:16 ላይ የሚገኘው አገላለጽ በዕብራይስጥ ቋንቋ የሚሠራበት ዘይቤ ነው፤ በዚህ ዘይቤ መሠረት ጸሐፊው፣ በሁለተኛ ደረጃ የተጠቀሰውን ቁጥር ለማጉላት ሲል ይህን ቁጥር መጀመሪያ ከተጠቀሰው ቁጥር ጋር ያነጻጽረዋል። እንዲህ ዓይነቱ አገላለጽ በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ብዙ ቦታዎች ላይ ተሠርቶበታል።—ኢዮብ 5:19፤ ምሳሌ 30:15, 18, 21

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ