የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 6/1 ገጽ 3
  • የኃጢአት ትርጉሙ ጠፍቶብን ይሆን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የኃጢአት ትርጉሙ ጠፍቶብን ይሆን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሰዎች ስለ ኃጢአት ያላቸውን አመለካከት የለወጠው ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ሰዎች የሚሞቱት ለምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • “ሰባት ቀሳፊ ኃጢአቶች” አሉ?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ኃጢአት የሌለበት ዓለም እንዴት ይገኛል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 6/1 ገጽ 3

የኃጢአት ትርጉሙ ጠፍቶብን ይሆን?

ከቅርብ ዓመታት በፊት ቤተ ክርስቲያን የሚያዘወትሩ ሰዎች ሰባኪያቸው “ሰባት ቀሳፊ ኃጢአቶች” ተብለው የሚታወቁትን ዝሙትን፣ ሆዳምነትን፣ ስስትን፣ ስንፍናን፣ ቁጣን፣ ቅናትንና ኩራትን ድምፁን ከፍ አድርጎ ሲያወግዝ መስማታቸው የተለመደ ነበር። ሰባኪው ኃጢአት መሥራት የሚያስከትላቸውን መዘዞች ደግሞ ደጋግሞ እየገለጸ አድማጮቹ ንስሐ እንዲገቡ ያስጠነቅቅ ነበር። “በአሁኑ ጊዜ” ግን አንድ ጸሐፊ እንደተናገሩት “አብዛኞቹ ሃይማኖታዊ ሰባኪዎች አድማጮቻቸውን ቅር ላለማሰኘት ሲሉ ስለ ኃጢአት አያነሱም፤ ከዚህ ይልቅ የሚያተኩሩት አድማጮቻቸውን ‘ደስ በሚያሰኙ’ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ነው።”

አንዳንድ የጋዜጣ አምድ አዘጋጆችም እንዲህ ያለ አዝማሚያ መኖሩን አስተውለዋል። ከተለያዩ ጋዜጣዎች ላይ ከተወሰዱት ሐሳቦች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦

▪ “ስለ ኃጢአት፣ ንስሐ ስለ መግባትና ስለ መዳን ይቀርብ የነበረው የድሮ ስብከት ቀርቶ ለራስ ከፍ ያለ ግምት ማዳበርንና ራስን መውደድን የሚያበረታታ ስብከት በቦታው ተተክቷል።”—ስታር ቤከን፣ አሽተብዩለ፣ ኦሃዩ

▪ “ሰዎች ስለ ኃጢአት መጨነቅ አቁመዋል።”—ኒውስዊክ

▪ “‘አምላክ ከእኔ ምን ይፈልጋል?’ ብለን መጠየቅ አቁመን ‘አምላክ ምን ሊያደርግልኝ ይችላል?’ ማለት ጀምረናል።”—ቺካጎ ሰን-ታይምስ

የተለያየ ባህል፣ ሃይማኖትና ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ተቻችለው በሚኖሩበት በዛሬው ጊዜ ሰዎች አንድን ነገር ከሥነ ምግባር አንጻር ትክክል ነው አይደለም ብሎ መናገር ይከብዳቸዋል። የሌሎች ሰዎችን ሥነ ምግባር ትክክል አይደለም ብሎ መናገር ጨዋነት እንደጎደለው ተግባር ተደርጎ ይታያል። እንዲያውም ከባድ ኃጢአት የሚመስለው አንድ ሰው የሚያደርገው ነገር ትክክል አይደለም ብሎ መፍረድ ነው። በመሆኑም እንደሚከተለው ያለ አመለካከት እየተስፋፋ ነው፦ ‘አንተ የምታምንበት ነገር ለአንተ ጥሩ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም አስተሳሰብህን ሌሎች እንዲቀበሉት ለመጫን መሞከር የለብህም። አሁን አሁን ሰዎች ሕይወታቸውን የሚመሩበት የተለያየ የሥነ ምግባር መሥፈርት አላቸው። አንድ ሰው እሱ ብቻ ትክክል እንደሆነ አድርጎ ሊናገር አይችልም። የሌሎች ሰዎች አመለካከትም የአንተን ያህል ትክክል ናቸው።’

እንዲህ ያሉ አመለካከቶች በሰዎች የቃላት አጠቃቀም ላይ ለውጥ አምጥተዋል። “ኃጢአት” የሚለው ቃል ከባድ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሲጠቀስ አይሰማም። ሰዎች አንድ ወንድና አንዲት ሴት በሕግ ሳይጋቡ አብረው ቢኖሩ “አብረው እየኖሩ ነው” እንጂ “ኃጢአት እየሠሩ ነው” አይሉም። ሁለት ሰዎች ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት ቢፈጽሙ ማንም ሰው “ግንኙነት አላቸው” እንጂ “ዝሙት” እየፈጸሙ ነው አይልም። እንዲሁም ግብረ ሰዶም መፈጸም እንደ ከባድ ኃጢአት መታየቱ ቀርቷል።

ሰዎች “የተለመደ ነገር” አድርገው የሚቀበሉት ወይም “ኃጢአት” ብለው የሚያወግዙት ነገር እንደተለወጠ ምንም ጥርጥር የለውም። ሆኖም የሰዎች አስተሳሰብ የተለወጠው ለምንድን ነው? ኃጢአትን በተመለከተ የተለወጠ ነገር ይኖር ይሆን? ስለ ኃጢአት ምንም ዓይነት አመለካከት ቢኖርህ ለውጥ አያመጣም?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ