የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 128
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንጽሔ ይናገራል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንጽሔ ይናገራል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መንጽሔ
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • መጽሐፍ ቅዱስን ልታምንበት ትችላለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ሞት
    ንቁ!—2014
  • ሙታንን ልትረዳቸው ትችላለህ?
    ንቁ!—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 128
አንድ ሠዓሊ ያዘጋጀው የመንጽሔ ንድፍ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንጽሔ ይናገራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አይናገርም። “መንጽሔ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ አይገኝም፤ በተጨማሪም የሞቱ ሰዎች ነፍስ በመንጽሔ እንደሚነጻ አያስተምርም።a መጽሐፍ ቅዱስ ሞትንና ሕይወትን አስመልክቶ ምን እንደሚያስተምርና ይህም ከመንጽሔ ትምህርት የተለየ የሆነው እንዴት እንደሆነ እንመልከት።

  • አንድን ሰው ከኃጢአት የሚያነጻው በኢየሱስ ደም ላይ ያለው እምነት እንጂ መንጽሔ ተብሎ በሚጠራ ቦታ የሚያሳልፈው ጊዜ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ “የልጁ [የአምላክ ልጅ] የኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” ይላል። በተጨማሪም ‘ኢየሱስ ክርስቶስ በገዛ ደሙ አማካኝነት ከኃጢአታችን ነፃ አውጥቶናል’ በማለት ይናገራል። (1 ዮሐንስ 1:7፤ ራእይ 1:5) ኢየሱስ “በብዙ ሰዎች ምትክ ሕይወቱን ቤዛ” አድርጎ በመስጠት የኃጢአታቸውን ዋጋ ከፍሏል።—ማቴዎስ 20:28

  • የሞቱ ሰዎች ምንም ነገር አያውቁም። “ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁም።” (መክብብ 9:5) የሞተ ሰው ምንም ዓይነት ስሜት ስለሌለው በመንጽሔ እሳት ሊነጻ አይችልም።

  • አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ለኃጢአቱ አይቀጣም። መጽሐፍ ቅዱስ “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው” እንዲሁም “የሞተ ከኃጢአቱ ነፃ ወጥቷል” በማለት ይናገራል። (ሮም 6:7, 23) ሞት ለኃጢአት ተመጣጣኝና የተሟላ ቅጣት ነው።

መንጽሔ ምንድን ነው?

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እንደምታስተምረው መንጽሔ ኃጢአታቸው ይቅር ሳይባል የሞቱ ነፍሳት ይቅርታ የሚያገኙበትና የሚነጹበት ቦታ ወይም ሁኔታ ነው።b ካቴኪዝም ኦቭ ዘ ካቶሊክ ቸርች እንደሚናገረው ይህ የመንጻት ሂደት “በሰማይ ያለውን ደስታ ለማግኘት የግድ አስፈላጊ የሆነውን ቅድስና ለሟሟላት” ያስችላል። ካቴኪዝም አክሎም “የቤተ ክርስቲያኗ ልማድ . . . ስለሚያነጻ እሳት ይናገራል” ይላል፤ ከዚህ ርዕስ ጋር ተያይዞ የቀረበው ሥዕል ይህን የሚያሳይ ነው። ይሁንና ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አይደለም።

የመንጽሔ ትምህርት የመጣው ከየት ነው?

የጥንቶቹ ግሪካውያን በሊምቦ እና በመንጽሔ ያምኑ ነበር። ይህ የግሪካውያን ፍልስፍና ተጽእኖ ያሳደረበት የእስክንድርያው ክሌመንት፣ የሞቱ ሰዎች ከኃጢአታቸው የሚነጹት በእሳት ነው ሲል ተናግሯል። ዘ ሂስትሪ ኦፍ ክርስቲያን ዶክትሪንስ የተባለው መጽሐፍ እንደሚናገረው ከሆነ ግን የመንጽሔ እሳት የተረጋገጠ ነገር እንደሆነ ለማሳመን የሞከሩት ታላቁ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ግሪጎሪ ናቸው። ይኸው መጽሐፍ አክሎም ከ590 እስከ 604 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩትን ግሪጎሪን ‘የመንጽሔ ትምህርት አባት’ ሲል ጠርቷቸዋል። የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የመንጽሔን ትምህርት በይፋ የተቀበለችው በሊዮን (1274) እንዲሁም በፍሎረንስ (1439) በተደረጉት ጉባኤዎች ላይ ሲሆን በ1547 በትሬንት በተደረገው ጉባኤ ላይ ደግሞ በድጋሚ ተቀብላዋለች።

a ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒድያ ሁለተኛ እትም ገጽ 824ን ተመልከት።

b ኦርፊየስ ኤ ጀነራል ሂስትሪ ኦፍ ሪልጅን የተባለው መጽሐፍ ስለ መንጽሔ ሲናገር “በወንጌሎች ውስጥ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገር አንድ ቃል እንኳ አይገኝም” ብሏል። በተመሳሳይም ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒድያ “በአጠቃላይ፣ ካቶሊክ ስለ መንጽሔ የምታስተምረው ትምህርት በቅዱሳን ጽሑፎች ላይ ሳይሆን በወግ ላይ የተመሠረተው ነው” ይላል።—ሁለተኛ እትም ጥራዝ 11 ገጽ 825

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ