የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwwd ርዕስ 31
  • የሃሚንግበርድ ምላስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሃሚንግበርድ ምላስ
  • ንድፍ አውጪ አለው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሃሚንግበርድ ምላስ
    ንቁ!—2010
  • አበቦችን የሚስመው ወፍ
    ንቁ!—1999
  • አንደበታችሁን በመቆጣጠር ፍቅርና አክብሮት አሳዩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • የማልፈልገውን ነገር የምናገረው ለምንድን ነው?
    የወጣቶች ጥያቄ
ለተጨማሪ መረጃ
ንድፍ አውጪ አለው?
ijwwd ርዕስ 31
ሃሚንግበርድ ምላሷን ዘርግታ የአበባ ማር ስትቀስም።

Moment/Robert D. Barnes via Getty Images

ንድፍ አውጪ አለው?

የሃሚንግበርድ ምላስ

ሃሚንግበርድ በምላሷ የአበባ ማር የምትቀስመው ካፒለሪ አክሽን ተብሎ በሚጠራው ሂደት እንደሆነ ሳይንቲስቶች ያምኑ ነበር፤ ይህም ፈሳሽ ነገር በቀጭን ቧንቧ ውስጥ ወደ ላይ እየተሳሳበ እንዲሄድ የሚያደርግ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው። ይሁንና ወፏ ከዚህም ይበልጥ ቀልጣፋና ኃይል ቆጣቢ ዘዴ እንደምትጠቀም የቅርብ ጊዜ የምርምር ውጤቶች አሳይተዋል።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ የሃሚንግበርድ ምላስ የአበባ ማር ውስጥ ሲገባ ለሁለት ይሰነጠቃል። እያንዳንዱ ስንጥቅ ጫፉ ላይ ክርክር አለው። ክርክሮቹ የተዘጉ ቀዳዶች አሏቸው። ምላሷ ወደ ፈሳሹ ሲገባ ቀዳዳዎቹ ይከፈታሉ፤ ተጠቅልሎ የነበረው የምላሷ ጫፍም ይዘረጋል። ይህም ፈሳሹን በአንዴ ላስ አድርጋ ለማውጣት ያስችላታል፤ ይህ ፈሳሹን ወደ ላይ ለመምጠጥ ከመሞከር የተሻለ ዘዴ ነው። ምላሷ ከፈሳሹ ሲወጣ ወዲያውኑ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ይመለሳል፤ የምላሷ ጫፍ ላይ ያሉት ቀዳዳዎች የአበባ ማሩን እንዳቆሩ ይዘጋሉ።

ምስሎች፦ ሃሚንግበርድ ምላሷን ዘርግታ የአበባ ማር ስትቀስም። ውስጠኛው ምስል፦ 1. ምላሷ ወደ አበባው ማር ሲገባ። 2. ለሁለት የተሰነጠቀው ምላሷ ጫፉ ላይ ባሉት ክርክሮች አማካኝነት የአበባውን ማር ይዞ ሲወጣ።

ተመራማሪዎቹ አሌሃንድሮ ሪኮ ጌቫራ፣ ታይ ሺ ፋን እና ማርጋሬት ሩቤጋ እንዳሉት ከሆነ ጠቅላላ ሂደቱ “የአንድ ሰከንድ አንድ አሥረኛ እንኳ አይወስድም።” በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦ “ምላሷ አስገራሚ ቅልጥፍና እንዳለው ፈሳሽ መሳቢያ ማሽን ነው። . . . ፈሳሽ ውስጥ ሲገባና ሲወጣ በሚገርም ፍጥነት ቅርጹን የመቀየር ችሎታ አለው።”

ከዚህም ሌላ ወፏ የአበባ ማር ስትቀስም ከራሷ ኃይል መጠቀም አያስፈልጋትም። የምላሷ ጫፍ እንዲዘረጋና እንዲዘጋ የሚያደርገው፣ ፈሳሽ ውስጥ ሲገባና ሲወጣ የሚኖረው ንክኪ ነው።

ተመራማሪዎች፣ የሃሚንግበርድ ምላስ ባለው ፈሳሽን በፍጥነት የመውሰድ ችሎታ ላይ ምርምር እያደረጉ ነው፤ ይህ ንድፍ በሕክምና፣ በሮቦት ሥራና በሌሎች መስኮች ትልቅ አስተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚችል ይሰማቸዋል። ነዳጅ ወይም ሌሎች ፈሳሾችን ለማጽዳት በሚያገለግሉ መሣሪያዎች ንድፍ ላይም ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይታሰባል።

ሃሚንግበርድ ምላሷን ስትዘረጋ ተመልከት

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የተራቀቀው የሃሚንግበርድ ምላስ በዝግመተ ለውጥ የመጣ ነው ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ