የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • hf ክፍል 5 ገጽ 15-17
  • ከዘመዶቻችሁ ጋር በሰላም መኖር የምትችሉት እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዘመዶቻችሁ ጋር በሰላም መኖር የምትችሉት እንዴት ነው?
  • ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 1 ለዘመዶቻችሁ ተገቢ አመለካከት ይኑራችሁ
  • 2 አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ጥብቅ ሁኑ
  • አንዳችሁ ለሌላው ታማኝ ሁኑ
    ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ትዳራችሁ አስደሳች እንዲሆን የአምላክን መመሪያ ተከተሉ
    ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • የትዳር ጓደኛችሁን በአክብሮት መያዝ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ከሠርጋችሁ ቀን በኋላ
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
ለተጨማሪ መረጃ
ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
hf ክፍል 5 ገጽ 15-17
አንዲት አማት፣ ምራቷ ምግብ ከምታበስልበት መንገድ ጋር በተያያዘ ነቀፋ አዘል በሆነ መንገድ ስትመለከታት

ክፍል 5

ከዘመዶቻችሁ ጋር በሰላም መኖር የምትችሉት እንዴት ነው?

“ደግነትን፣ ትሕትናን፣ ገርነትንና ትዕግሥትን ልበሱ።”—ቆላስይስ 3:12

ትዳር ውስጥ ስትገባ አዲስ ቤተሰብ ትመሠርታለህ። ወላጆችህን ምንጊዜም የምትወዳቸውና የምታከብራቸው ቢሆንም ካገባህ በኋላ ግን በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ የምትበልጥብህ የትዳር ጓደኛህ ናት። የሁለታችሁም ወላጆችም ሆነ ሌሎች ዘመዶች ይህን ሐቅ መቀበል ሊከብዳቸው ይችላል። ይሁን እንጂ አዲሱን ቤተሰባችሁን ለማጠናከር ስትጥሩ ከሁለታችሁም ወላጆችና ዘመዶች ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖራችሁ በማድረግ ረገድ ሚዛናችሁን መጠበቅ እንድትችሉ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ሊረዷችሁ ይችላሉ።

1 ለዘመዶቻችሁ ተገቢ አመለካከት ይኑራችሁ

አንድ ባልና ሚስት ሲያወሩ፤ ባልና ሚስት ለወላጆቻቸው ስጦታ ሲሰጡ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “አባትህንና እናትህን አክብር።” (ኤፌሶን 6:2) ትልቅ ሰው ብትሆንም ምንጊዜም ወላጆችህን ማክበር ያስፈልግሃል። የትዳር ጓደኛህም ለወላጆቿ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልጋት መዘንጋት የለብህም። “ፍቅር አይቀናም።” በመሆኑም የትዳር ጓደኛህ ከወላጆቿ ጋር በመቀራረቧ ልትሰጋ አይገባም።—1 ቆሮንቶስ 13:4፤ ገላትያ 5:26

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • “ቤተሰቦችሽ ሁልጊዜ ይንቁኛል” ወይም “እናትህ እኔ የማደርገው ነገር ሁሉ በፍጹም አያስደስታትም” እንደሚሉት ያሉ አነጋገሮችን ከመጠቀም ተቆጠቡ

  • ነገሮችን በትዳር ጓደኛችሁ ቦታ ሆናችሁ ለማየት ሞክሩ

2 አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ጥብቅ ሁኑ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” (ዘፍጥረት 2:24) ትዳር ከመሠረታችሁም በኋላ ወላጆቻችሁ እናንተን የመንከባከብ ኃላፊነት እንዳለባቸው ሊሰማቸው ይችላል፤ በመሆኑም ከሚገባው በላይ በትዳራችሁ ውስጥ ለመግባት ይሞክሩ ይሆናል።

በዚህ ረገድ ገደብ ማበጀትና ይህንንም ፍቅር በሚንጸባረቅበት መንገድ ለወላጆቻችሁ ማሳወቁ የእናንተ ኃላፊነት ነው። ወላጆቻችሁን የሚያስከፋ ነገር ሳትናገሩ ጉዳዩን በግልጽና በማያሻማ መንገድ ልታሳውቋቸው ትችላላችሁ። (ምሳሌ 15:1) ትሕትና፣ ገርነትና ትዕግሥት ከወላጆቻችሁም ሆነ ከሌሎች ዘመዶቻችሁ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራችሁና “እርስ በርሳችሁ በፍቅር በመቻቻል” እንድትኖሩ ይረዷችኋል።—ኤፌሶን 4:2

አንድ ባልና ሚስት ከወላጆቻቸው ጋር ጊዜ ሲያሳልፉ

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • ዘመዶቻችሁ በሕይወታችሁ ውስጥ ከሚገባው በላይ ጣልቃ እየገቡ እንደሆነ ከተሰማህ ጉዳዩን ተረጋግታችሁ ባላችሁበት ሰዓት ከትዳር ጓደኛህ ጋር ተወያዩበት

  • እነዚህን ጉዳዮች እንዴት መፍታት እንደምትችሉ ተወያይታችሁ ወስኑ

ወላጆቻችሁን ለመረዳት ጣሩ

የወላጆቻችሁን ስሜትና አመለካከታቸውን መረዳታችሁ አስፈላጊ ነው። በትዳራችሁ ውስጥ የሚገቡት ሊጎዷችሁ ብለው ሳይሆን ከልብ ስለሚያስቡላችሁ ነው። ወላጆቻችሁ፣ አንተና የትዳር ጓደኛህ የራሳችሁ ቤተሰብ እንዳላችሁ መቀበል ይከብዳቸው ይሆናል። እንዲያውም እንደተተዉ ሊሰማቸው ይችላል። ይሁን እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች በመከተልና ግልጽ የሐሳብ ልውውጥ በማድረግ ትዳራችሁን አደጋ ላይ ሳትጥሉ ወላጆቻችሁን አክብራችሁ መኖር ትችላላችሁ።

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  • የባለቤቴ ወላጆች ስለ ትዳራችን ለማወቅ ቢፈልጉ የሚያስገርም ያልሆነው ለምንድን ነው?

  • ለወላጆቼ አክብሮት እያሳየሁ ለትዳር ጓደኛዬ አንደኛ ቦታ መስጠት የምችለው እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ