መዝሙር 126
ነቅተህ ኑር፣ ጸንተህ ቁም፣ በርታ
በወረቀት የሚታተመው
1. ነቅተህ ኑር፣ ጸንተህ ቁም፣ በርታ፤
በአቋምህም ጽና።
ደፋር፣ ወንድ ሁን፣ አትበገር፤
ድል ቀርቧል አትሸበር።
የጌታን ት’ዛዝ ተከትለን፣
ከሱ ጎን እንሰለፋለን።
(አዝማች)
ነቅተህ ኑር፣ ጽና፣ ሁሌም በርታ!
አትዘናጋ ላፍታ!
2. ነቅተህ ኑር፣ ከቶ አትፍዘዝ፤
ፈጣን ሁን ለመታዘዝ።
ጌታ በታማኙ ባሪያ
ስማ ሲሰጥ መመሪያ።
እረኞች ሲመክሩህ ስማቸው፤
የመንጋው ጠባቂዎች ናቸው።
(አዝማች)
ነቅተህ ኑር፣ ጽና፣ ሁሌም በርታ!
አትዘናጋ ላፍታ!
3. ነቅተን እንጠብቅ አንድ ሆነን፤
ለምሥራቹ ቆመን።
እናውጃለን በጽናት፤
ቢቃወመንም ጠላት።
የሁላችንም ድምፅ ይሰማ፤
የይሖዋ ቀን ቀርቧልና!
(አዝማች)
ነቅተህ ኑር፣ ጽና፣ ሁሌም በርታ!
አትዘናጋ ላፍታ!