መዝሙር 121
እርስ በርስ እንበረታታ
በወረቀት የሚታተመው
1. እርስ በርስ ስንበረታታ፣
ታማኝ ሆነን ለማገልገል፣
ዝምድናችን ይጠናከራል፤
ሰላም ኅብረት ይኖረናል።
በኛ መካከል ያለው ፍቅር፣
እያንዳንዱን ሰው ያጸናል።
ጉባኤ ጥበቃ ያስገኛል፤
በዚያ መሆን ያረጋጋል።
2. በተገቢው ወቅት ሲነገር ቃል፣
እንዴት ’ሚያጽናና ይሆናል!
እንዲህ ዓይነት ቃል እንሰማለን፣
ከታማኝ ወዳጆቻችን።
ደስ ይለናል አብረን ስንሠራ፣
ስላለን አንድ ዓይነት ተስፋ።
እርስ በርስ እንበረታታ፤
ሁሉም ሸክሙን እንዲወጣ።
3. በእምነት ዓይን ስለሚታየን
መቅረቡ የይሖዋ ቀን፣
ከሕይወት መንገድ እንዳንወጣ
መሰብሰብ አለብን አብረን።
ዘላለም ’ናገለግላለን፣
ካምላክ ሕዝቦች ጋር አንድ ሆነን።
ንጹሕ አቋማችን እንዳይጎድፍ
እርስ በርስ እንደጋገፍ።
(በተጨማሪም ሉቃስ 22:32ን፣ ሥራ 14:21, 22ን፣ ገላ. 6:2ን እና 1 ተሰ. 5:14ን ተመልከት።)