መዝሙር 43
ነቅተህ ኑር፣ ጸንተህ ቁም፣ በርታ
በወረቀት የሚታተመው
1. ነቅተህ ኑር፣ ጸንተህ ቁም፣ በርታ፤
በአቋምህም ጽና።
ደፋር ወንድ ሁን አትበገር፤
ድል ቀርቧል አትሸበር።
የጌታን ት’ዛዝ ተከትለን፣
ከሱ ጎን እንሰለፋለን።
(አዝማች)
ነቅተህ ኑር፣ ጽና፣ ሁሌም በርታ!
አትዘናጋ ላፍታ!
2. ነቅተህ ኑር፣ ከቶ አትፍዘዝ፤
ፈጣን ሁን ለመታዘዝ።
ጌታ ሲሰጥህ መመሪያ፣
ስማ ታማኙን ባሪያ።
እረኞች ሲመክሩህ ስማቸው፤
ጠባቂዎች ናቸው የመንጋው።
(አዝማች)
ነቅተህ ኑር፣ ጽና፣ ሁሌም በርታ!
አትዘናጋ ላፍታ!
3. ነቅተን እንጠብቅ አንድ ሆነን፤
ለምሥራቹ ቆመን።
እናውጃለን በጽናት፤
ቢቃወመንም ጠላት።
የሁላችንም ድምፅ ይሰማ፤
የይሖዋ ቀን ቀርቧልና!
(አዝማች)
ነቅተህ ኑር፣ ጽና፣ ሁሌም በርታ!
አትዘናጋ ላፍታ!