መዝሙር 49
የይሖዋን ልብ ማስደሰት
በወረቀት የሚታተመው
1. አምላክ፣ ላንተ ቃል ገብተናል፤
ልናመልክህ ወስነናል።
ስንመራ በጥበብህ፣
በኛ ደስ ይሰኛል ልብህ።
2. ምድር ያለው ታማኝ ባሪያህ፣
ያውጃል ታላቅ ስምህን፤
በጊዜው ይመግበናል፤
ለሥራህ ያስታጥቀናል።
3. ’ባክህ ስጠን መንፈስህን፤
እንድንኖር ታማኝ ሆነን፤
ከልብ እንድናወድስህ፣
ሁሌም ደስ እንድናሰኝህ።
(በተጨማሪም ማቴ. 24:45-47ን፣ ሉቃስ 11:13ን እና 22:42ን ተመልከት።)