መዝሙር 68
የመንግሥቱን ዘር መዝራት
በወረቀት የሚታተመው
1. እናንት ጌታ የጋበዛችሁ፣
ወደ መስኩ የጠራችሁ፣
ጥሪውን ሰምታችሁ ታዘዙ፤
ይረዳችኋል፣ አትፍሩ።
በቅኖች ልብ ውስጥ ቃሉን ብትዘሩ
ዘሩ አይቀርም ማፍራቱ።
ስለዚህ በርቱ፣ በትጋት ስበኩ።
አይዟችሁ፣ ተስፋ አትቁረጡ።
2. ስኬት ማግኘታችሁ ’ሚመካው
ባብዛኛው በ’ናንተ ላይ ነው።
ቅኖች ልባቸው እንዲነካ
እናንተም ድርሻ አላችሁ።
ፈተናን፣ ተቃውሞን እንዲወጡ
እርዷቸው እንዲበረቱ።
እድገት ሲያደርጉ፣ የ’ውነት ዘር ሲያፈራ፣
ልባችሁ ይሞላል በደስታ።
(በተጨማሪም ማቴ. 13:19-23ን እና 22:37ን ተመልከት።)