መዝሙር 40
አስቀድማችሁ መንግሥቱን ፈልጉ
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ የመሠረተው፣
እሱን የሚያስደስተው፣
ችግሮችን የሚፈታው፣
የክርስቶስ መንግሥት ነው።
(አዝማች)
በቅድሚያ ፈልግ መንግሥቱን፤
ምንጊዜም ቢሆን ጽድቁን።
ክብሩንም ተናገር ለሰው፤
ታማኝ ሁን፣ አገልግለው።
2. ለምን ለነገ ’ንጨነቅ?
‘እንራብ ይሆን?’ ብለን።
ባምላክ ይሟላል የቀረው፤
ካስቀደምን መንግሥቱን።
(አዝማች)
በቅድሚያ ፈልግ መንግሥቱን፤
ምንጊዜም ቢሆን ጽድቁን።
ክብሩንም ተናገር ለሰው፤
ታማኝ ሁን፣ አገልግለው።
3. ምሥራቹን ንገራቸው፤
ያስተውሉት እርዳቸው።
ይሖዋንና መንግሥቱን
እንዲያደርጉ ተስፋቸው።
(አዝማች)
በቅድሚያ ፈልግ መንግሥቱን፤
ምንጊዜም ቢሆን ጽድቁን።
ክብሩንም ተናገር ለሰው፤
ታማኝ ሁን፣ አገልግለው።
(በተጨማሪም መዝ. 27:14ን፣ ማቴ. 6:34፤ 10:11, 13ን እና 1 ጴጥ. 1:21ን ተመልከት።)