መዝሙር 18
የአምላክ ታማኝ ፍቅር
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ ፍቅር ነው፤
ደስ የሚለን ለዚህ ነው።
ፍቅር ገፍቶት ላከልን፣
ልጁ ቤዛ እንዲሆን፤
ከኃጢያት እንድንድን፣
ሕይወትም እንድናገኝ።
(አዝማች)
ኑ ’ናንት የተጠማችሁ፣
የሕይወት ውኃ ጠጡ።
እናንት የተጠማችሁ፣
ፍቅሩን ተመልከቱ።
2. ይሖዋ ፍቅር ነው፤
ሥራውም ምሥክር ነው።
አሳይቶናል ፍቅሩን፣
ለኛ በማንገሥ ልጁን።
ሊፈጽም ቃል ኪዳኑን፣
መሠረተ መንግሥቱን።
(አዝማች)
ኑ ’ናንት የተጠማችሁ፣
የሕይወት ውኃ ጠጡ።
እናንት የተጠማችሁ፣
ፍቅሩን ተመልከቱ።
3. ይሖዋ ፍቅር ነው፤
በፍቅሩም እንምሰለው።
እንርዳቸው ገሮችን
እንዲያገኙ መንገዱን።
መጽናናት እንዲችሉ፣
እውነት ይድረስ ለሁሉ።
(አዝማች)
ኑ ’ናንት የተጠማችሁ፣
የሕይወት ውኃ ጠጡ።
እናንት የተጠማችሁ፣
ፍቅሩን ተመልከቱ።