መዝሙር 5
ምሳሌያችን የሆነው ክርስቶስ
በወረቀት የሚታተመው
(ሮም 5:8)
1. ይሖዋ አሳየን እጅግ ታላቅ ፍቅሩን፣
ለሰው ዘር ሰጠ ተወዳጅ ልጁን።
ክርስቶስ ለኛ ሲል ሕይወቱን ሠዋልን፤
ዘላለም መኖር እውን ሆነልን።
2. ዘወትር ጸልዩ ብሎናል ክርስቶስ፤
የይሖዋ ’ምላክ ስም እንዲቀደስ፣
መንግሥቱ ’ንዲመጣ፣ ፈቃዱ ’ንዲፈጸም፣
የ’ለት ምግብ እንዲሰጠን ሁሌም።
3. ለተከታዮቹ እፎይታ ሰጣቸው፤
ያምላክን እውነት አስተማራቸው።
ዘወትር እናውጅ የመንግሥቱን እውነት፣
እናገኛለን ደስታ፣ በረከት።
(በተጨማሪም ማቴ. 6:9-11ን፣ ዮሐ. 3:16፤ 6:31-51ን እና ኤፌ. 5:2ን ተመልከት።)