መዝሙር 55
መጨረሻ የሌለው ሕይወት
በወረቀት የሚታተመው
1. ይታይህ ባዲስ ዓለም፤
ሁሉም ሲኖር ዘላለም።
ሐዘን፣ ሥቃይ ተረስቶ፤
ሰላም፣ ደስታ ሰፍኖ።
(አዝማች)
እጅግ ደስ ይበልህ!
ይህን ቀን ታያለህ።
መጨረሻ የሌለው፣
ሕይወት ልታገኝ ነው!
2. እርጅና ይወገዳል፤
ልጅነት ይመለሳል።
ነፃ ስንሆን ከችግር፣
አይኖር ለቅሶ፣ ሽብር።
(አዝማች)
እጅግ ደስ ይበልህ!
ይህን ቀን ታያለህ።
መጨረሻ የሌለው፣
ሕይወት ልታገኝ ነው!
3. ሁላችን ገነት ገብተን፣
በደስታ እ’ኖራለን።
ለዘላለም ይሖዋን
’ናመሰግናለን።
(አዝማች)
እጅግ ደስ ይበልህ!
ይህን ቀን ታያለህ።
መጨረሻ የሌለው፣
ሕይወት ልታገኝ ነው!