መዝሙር 35
አምላክ ላሳየን ትዕግሥት አመስጋኝ መሆን
በወረቀት የሚታተመው
1. አምላካችን፣ ታላቅ ነው ኃይልህ፤
ጽድቅን እጅግ ትወዳለህ።
ግን በምድር ክፋት ነግሷል፤
በዚ’ም ልብህ በጣም አዝኗል።
አትዘገይም፣ ለሰው ባይመስልም፤
ጊዜው ቀርቧል፣ ክፋት ይጠፋል።
በአንተ ላይ እምነት አለን፤
ለት’ግሥትህ አመስጋኞች ነን።
2. እናውቃለን ሺህ ዓመት ላንተ፤
እንዳንድ ቀን እንደሆነ።
ታላቁ ቀንህ ይመጣል፤
አይዘገይም፣ ጊዜው ቀርቧል።
ኃጢያትን ሁሉ ብትጠላም፣
ሰው ሲመለስ ግን ደስ ይልሃል።
አንተን ተስፋ ’ናደርጋለን፤
ስምህንም ’ናወድሳለን።
(በተጨማሪም ሉቃስ 15:7ን እና 2 ጴጥ. 3:8, 9ን ተመልከት።)