የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/14 ገጽ 2
  • አጋጣሚውን ትጠቀሙበታላችሁ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አጋጣሚውን ትጠቀሙበታላችሁ?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከሁሉ ለላቀው የአምላክ ስጦታ አድናቆታችንን መግለጽ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • አድናቆት እንዳለን እናሳይ—የመታሰቢያው በዓል ሚያዝያ 17 ይከበራል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • “ይህን ሁልጊዜ . . . አድርጉት”—የመታሰቢያው በዓል መጋቢት 27, 2004 (ሚያዝያ 5, 2012) ይከበራል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • “ክርስቶስ ያለው ፍቅር ግድ ይለናል”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
km 3/14 ገጽ 2

አጋጣሚውን ትጠቀሙበታላችሁ?

መጪው የመታሰቢያ በዓል አድናቆታችንን ለመግለጽ አጋጣሚ ይሰጠናል

1. የመታሰቢያው በዓል ምን ልዩ አጋጣሚ ይፈጥርልናል?

1 ሚያዝያ 14 የሚከበረው የመታሰቢያ በዓል ይሖዋ ላሳየን ጥሩነት ያለንን አድናቆት ለማሳደግ ብሎም በተግባር ለማሳየት ልዩ አጋጣሚ ይፈጥርልናል። በ⁠ሉቃስ 17:11-18 ላይ የሚገኘው ዘገባ ይሖዋና ኢየሱስ አመስጋኝ ስለ መሆን ያላቸውን አመለካከት ይጠቁማል። በታሪኩ ላይ ከተጠቀሱት ከሥጋ ደዌ የተፈወሱ አሥር ሰዎች መካከል ምስጋናውን ለመግለጽ የመጣው አንዱ ብቻ መሆኑ የሚያሳዝን ነው። የቤዛው ስጦታ ወደፊት ከማንኛውም በሽታ እንድንገላገል የሚያደርግ ከመሆኑም ሌላ የዘላለም ሕይወት እንድናገኝ ያስችለናል! ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ ለምናገኛቸው በረከቶች ሁሉ ይሖዋን በየዕለቱ እንደምናመሰግነው ጥርጥር የለውም! ታዲያ በቀጣዮቹ ሳምንታት አመስጋኝ መሆናችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

2. ለቤዛው ያለንን አድናቆት ማሳደግ የምንችለው እንዴት ነው?

2 አድናቆታችንን ማሳደግ፦ የአድናቆት ስሜት የሚመነጨው ከማሰብ ነው። ለቤዛው ያለንን አድናቆት ለማሳደግ እንዲረዳን ተብሎ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የምናነብበው ልዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም ተዘጋጅቶልናል፤ ይህ ፕሮግራም በተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም (እንግሊዝኛ) ተጨማሪ ክፍል B12፣ በየካቲት 1, 2011 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22-23፣ በቀን መቁጠሪያችን እና ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር በተባለው ቡክሌት ላይ ይገኛል። በፕሮግራሙ ላይ የሰፈሩትን መረጃዎች በቤተሰብ ሆናችሁ ለመወያየት ለምን አትሞክሩም? እንዲህ ማድረጋችን ለቤዛው ያለን አድናቆት እያደገ እንዲሄድ ያደርጋል። ይህ ደግሞ በአኗኗራችን ላይ በጎ ተጽዕኖ ይኖረዋል።—2 ቆሮ. 5:14, 15፤ 1 ዮሐ. 4:11

3. በመታሰቢያው በዓል ሰሞን ለቤዛው ያለንን አድናቆት ማሳየት የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

3 አድናቆታችንን ማሳየት፦ አድናቆት እንዳለን የሚታወቀው በተግባር ሲታይ ነው። (ቆላ. 3:15) ከሥጋ ደዌ ከተፈወሱት መካከል አመስጋኝ የነበረው ሰው ኢየሱስን ፈልጎ በማግኘት ምስጋናውን ገልጿል። በተጨማሪም እንዴት በተአምር እንደተፈወሰ ለሌሎች በግለት ተናግሮ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም። (ሉቃስ 6:45) እኛስ ለቤዛው ዝግጅት ያለን አድናቆት የመታሰቢያውን በዓል ለማስተዋወቅ በሚደረገው ዘመቻ በቅንዓት እንድንካፈል ያነሳሳናል? በመታሰቢያው በዓል ሰሞን ረዳት አቅኚ መሆን ወይም በአገልግሎት የምናደርገውን ተሳትፎ መጨመር አመስጋኝነታችንን የምንገልጽበት ሌላው ግሩም መንገድ ነው። የመታሰቢያው በዓል በሚከበርበት ምሽት ላይ ደግሞ እንግዶችን በመቀበል እንዲሁም ለጥያቄዎቻቸው መልስ ለመስጠት ራሳችንን በማቅረብ አድናቆት እንዳለን እናሳያለን።

4. ይህ የመታሰቢያ በዓል ካለፈ በኋላ እንዳይቆጨን ምን ማድረግ ይኖርብናል?

4 በዚህ ዓመት የምናከብረው የመታሰቢያ በዓል የመጨረሻችን ይሆን? (1 ቆሮ. 11:26) ስለዚህ ጉዳይ የምናውቀው ነገር የለም። ይሁን እንጂ አንድ የምናውቀው ነገር አለ፤ ይህ አጋጣሚ አንዴ ካለፈን አድናቆታችንን ለመግለጽ የሚያስችል ልዩ አጋጣሚም አብሮ ያልፋል። ታዲያ አጋጣሚውን ትጠቀሙበታላችሁ? አድናቆታችንን የሚገልጸው የአፋችን ቃልና የልባችን ሐሳብ ቤዛውን በልግስና የሰጠንን ይሖዋን የሚያስደስት እንዲሆን ምኞታችን ነው።—መዝ. 19:14

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ