መዝሙር 81
“እምነት ጨምርልን”
በወረቀት የሚታተመው
(ሉቃስ 17:5)
1. አምላክ ሆይ፣ ፍጹም ባለመሆናችን፣
ወደ ክፋት ያደላል ልባችን።
ይሖዋ ሆይ፣ ባንተ ላይ እምነት ማጣት፣
ነው ሳናውቀው የሚያጠምደን ኃጢያት።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ እምነትን ጨምርልን።
ታውቀዋለህ የሚያስፈልገንን።
መሐሪ ነህ፤ እምነትን ጨምርልን።
እናክብርህ በቃል፣ በሥራችን።
2. ሰው አይችልም ሊያስደስትህ ያለ’ምነት።
እምነት ወሮታ ’ንዳለው አንሳት።
እምነታችን ነው ጋሻ ከለላችን፤
ከቶ አንፈራም የወደፊቱን።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ እምነትን ጨምርልን።
ታውቀዋለህ የሚያስፈልገንን።
መሐሪ ነህ፤ እምነትን ጨምርልን።
እናክብርህ በቃል፣ በሥራችን።