መዝሙር 19
አምላክ የሰጠው የገነት ተስፋ
በወረቀት የሚታተመው
1. በክርስቶስ ሺህ ዓመት ግዛት፣
ትሆናለች ምድር ገነት።
ኃጢያት፣ በደል ይደመሰሳል፤
ሥቃይ፣ ሞትም ይወገዳል።
(አዝማች)
ምድርን ገነት ያደርጋታል፤
በእምነት ዓይን ይታየናል።
ተስፋው በቅርብ ይፈጸማል፤
ጌታ ’የሱስ ይታመናል።
2. ሙታን በቅርብ ተስፋ አላቸው፤
ይነሳሉ፣ ዓላማው ነው።
‘በገነት ውስጥ ትኖራለህ’ ሲል
የአምላክ ልጅ ተስፋ ሰጥቷል።
(አዝማች)
ምድርን ገነት ያደርጋታል፤
በእምነት ዓይን ይታየናል።
ተስፋው በቅርብ ይፈጸማል፤
ጌታ ’የሱስ ይታመናል።
3. ጌታ ’የሱስ ተስፋ ሰጥቶናል፤
የምድራችን ንጉሥ ሆኗል።
ይሖዋንም እናመስግነው፤
በየ’ለቱ ’ናወድሰው።
(አዝማች)
ምድርን ገነት ያደርጋታል፤
በእምነት ዓይን ይታየናል።
ተስፋው በቅርብ ይፈጸማል፤
ጌታ ’የሱስ ይታመናል።
(በተጨማሪም ማቴ. 5:5፤ 6:10ን እና ዮሐ. 5:28, 29ን ተመልከት።)