መዝሙር 76
ይሖዋ የሰላም አምላክ ነው
በወረቀት የሚታተመው
1. የሰላም አምላክ ነህ፤
አይነጥፍም ፍጹም ፍቅርህ።
ስጠን ሰላም፣ መረጋጋት፤
ፍሬ ’ናፍራ በብዛት።
ምክርህ አስፈለገን፤
በልጅህ ሕያው ሆንን።
ከአ’ምሮ የላቀውን፣
ሰላምን ’ባክህ ስጠን።
2. ዓለም ሰላም ቢሻም፣
መከራን ዘርቶ ያጭዳል።
የመረጥከው ውድ ሕዝብህ ግን፣
በሰላም ውሎ ያድራል።
ስናውቅ ፈቃድህን፣
ስንፈጽም ቃላችንን፣
ጥረታችንን ባርክልን፤
አብዛልን ሰላምህን።
3. መሪ ነው መንፈስህ፤
ይሰጣል ቃልህ ብርሃን።
በዚህ ጨለማ ዓለም ውስጥ፣
ጠባቂም፣ መሪም ሆንከን።
እንደ ማለዳ ጠል፣
ሰላምህ ያረጋጋን።
አ’ምሮና ልባችንን፣
አምላክ ሆይ ጠብቅልን።
(በተጨማሪም መዝ. 4:8ን፣ ፊልጵ. 4:6, 7ን እና 1 ተሰ. 5:23ን ተመልከት።)