ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢዮብ 11-15
ኢዮብ በትንሣኤ ተስፋ ላይ እምነት ነበረው
ኢዮብ አምላክ እሱን ከሞት የማስነሳት ችሎታ እንዳለው ተናገረ
ኢዮብ፣ አምላክ ከሞት እንደሚያስነሳው ያለውን እምነት ለመግለጽ ዛፍን ምናልባትም የወይራ ዛፍን እንደ ምሳሌ ተጠቅሟል
የወይራ ዛፍ ሥሩን በስፋት ስለሚዘረጋ ግንዱ ቢደርቅም እንኳ ዛፉ ሊያንሠራራ ይችላል። ሥሮቹ እስካልሞቱ ድረስ ዛፉ እንደገና ያቆጠቁጣል
ከከባድ ድርቅ በኋላ ዝናብ ሲጥል፣ ደርቆ የነበረ የወይራ ዛፍ ጉቶ እንደገና ሊያንሰራራ ይችላል፤ ከዛፉ ሥሮች ላይ ቀንበጥ ማቆጥቆጥ ስለሚጀምር ዛፉ ‘እንደ አዲስ ተክል ቅርንጫፎች ያወጣል’