መዝሙር 111
አምላክ ይጣራል
በወረቀት የሚታተመው
1. የሰው ሕይወት ጠፊ ነው እንፋሎት፤
ዛሬ ታይቶ ለቅጽበት።
ስንሞት ሁሉም ነገር ያከትማል፤
እንባ፣ ሐዘን ይነግሣል።
ሰው ይነሳል ወይ አንዴ ከሞተ?
አምላክ ቃል ገብቶልናል፦
(አዝማች)
ይጣራል፤ ይመልሳሉ፤
በሕይወት ይኖራሉ።
የ’ጁ ሥራዎች ናቸው፤
ይጓጓል ሊያስነሳቸው።
እንግዲያው እምነት ይኑርህ፤
ይሖዋ ’ንደሚያስነሳህ።
የ’ጁ ሥራ ስለሆ’ን
ዘላለም እ’ኖራለን።
2. ያምላካችን ወዳጆች ቢሞቱም
በፍጹም አይረሱም።
ያንቀላፉ ባምላክ መዝገብ ያሉ፣
ቃል ገብቷል ይነቃሉ።
ከዚያም በገነት እንኖራለን
ዘላለም አብረናቸው።
(አዝማች)
ይጣራል፤ ይመልሳሉ፤
በሕይወት ይኖራሉ።
የ’ጁ ሥራዎች ናቸው፤
ይጓጓል ሊያስነሳቸው።
እንግዲያው እምነት ይኑርህ፤
ይሖዋ ’ንደሚያስነሳህ።
የ’ጁ ሥራ ስለሆ’ን
ዘላለም እ’ኖራለን።