የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች—መስከረም 2016
መስከረም 19-25
it-1 783 አን. 5
ዘፀአት
በዚህ መንገድ ይሖዋ ኃይሉን አስደናቂ በሆነ ሁኔታ በማሳየት ስሙ ከፍ ከፍ እንዲልና እስራኤላውያን ነፃ እንዲወጡ አደረገ። እስራኤላውያን ከጠላቶቻቸው አምልጠው በቀይ ባሕር ምሥራቃዊ ዳርቻ ላይ ሲደርሱ ሙሴ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ መዘመር ጀመረ፤ እህቱ የሆነችው ነቢዪቱ ሚርያምም አታሞ አንስታ ከወንዶቹ ጋር እየተቀባበለች ስትዘምር ሴቶቹ ሁሉ አታሞ እየመቱና እየጨፈሩ ተከተሏት። (ዘፀ 15:1, 20, 21) የእስራኤላውያን ጠላቶች ከዚህ በኋላ ጨርሶ ሊደርሱባቸው አይችሉም። ሕዝቡ ከግብፅ ሲወጡ ይሖዋ፣ ሰውም ሆነ እንስሳ ጉዳት እንዲያደርስባቸው አልፈቀደም፤ ውሻ እንኳ አልጮኸባቸውም ወይም ምላሱን አላሾለባቸውም። (ዘፀ 11:7) በዘፀአት መጽሐፍ ላይ የሚገኘው ዘገባ ፈርዖን ከሠራዊቱ ጋር እንደሰመጠ ባይገልጽም መዝሙር 136:15 ይሖዋ “ፈርዖንንና ሠራዊቱን ቀይ ባሕር ውስጥ ወረወረ” ይላል።
ከመስከረም 26–ጥቅምት 2
it-2 448
አፍ፣ አንደበት
ምግብን አኝኮ ወደ ሆድ እንዲልክ እንዲሁም ሰዎች ለመናገር እንዲጠቀሙበት ሲል አምላክ የሠራው የአካል ክፍል ነው። ሰዎች የመናገር ችሎታቸውን ተጠቅመው ምንጊዜም አምላክን ሊያወድሱት ይገባል። (መዝ 34:1፤ 51:15፤ 71:8፤ 145:21) መዝሙራዊው፣ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ይሖዋን እንዲያወድስ አበረታቷል፤ በመሆኑም የሰው ልጆች ሕይወት ማግኘት ከፈለጉ አፋቸውን ወይም አንደበታቸውን ይሖዋን ለማወደስ መጠቀም ይኖርባቸዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ በአምላክና በልጁ በልባችን ማመን ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ገልጿል። መዳን ለማግኘት እምነታችንን በይፋ መናገር አለብን።—መዝ 150:6፤ ሮም 10:10
ይሖዋ ከዓላማው እንዲሁም ፈጣሪ እንደመሆኑ መጠን ካለው መብትና ሥልጣን ጋር በሚስማማ መልኩ፣ በአገልጋዮቹ አንደበት ወይም አፍ ላይ ተገቢውን ቃል ያኖራል። ለነቢያቱ ይህን ያደረገው በተአምር ይኸውም እነሱን በመንፈሱ በመምራት ነበር። (ዘፀ 4:11, 12, 15፤ ኤር 1:9) እንዲያውም በአንድ ወቅት፣ መናገር የማትችል እንስሳ ማለትም አህያ እንድትናገር አድርጓል። (ዘኁ 22:28, 30፤ 2ጴጥ 2:15, 16) በዛሬው ጊዜም አምላክ ቃሉን በአገልጋዮቹ አፍ ላይ ያኖራል፤ ሆኖም እንዲህ የሚያደርገው እንደ ጥንቶቹ ነቢያት በተአምራዊ ሁኔታ በመንፈሱ መሪነት እንዲናገሩ በማድረግ ሳይሆን አገልጋዮቹ ለማንኛውም መልካም ሥራ በሚገባ እንዲታጠቁ በሚረዳቸውና በመንፈስ መሪነት በተጻፈው በቃሉ አማካኝነት ነው። (2ጢሞ 3:16, 17) አገልጋዮቹ፣ ክርስቶስ መጥቶ ምሥራቹን እንዲነግራቸው መጠበቅ ወይም ደግሞ የሚሰብኩትን መልእክት ከሌላ ምንጭ ለማግኘት መሞከር አያስፈልጋቸውም። የሚሰብኩት መልእክት በእጃቸው ነው፤ “ቃሉ ለአንተ ቅርብ ነው፤ ደግሞም በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው” ስለተባሉ መልእክቱ ተዘጋጅቶ እየጠበቃቸው ነው።—ሮም 10:6-9፤ ዘዳ 30:11-14
የሕይወት ወይም የሞት ኃይል አለው። በመሆኑም አንደበታችንን በተገቢው መንገድ መጠቀም ይኖርብናል፤ ይሖዋም እንዲህ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል። ቃሉ “የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ነው” ይላል። (ምሳሌ 10:11) በመሆኑም አፋችንን ወይም አንደበታችንን በጥንቃቄ መጠበቅ ይኖርብናል (መዝ 141:3፤ ምሳሌ 13:3፤ 21:23)፤ ምክንያቱም የሞኝ ሰው አንደበት ጥፋት ሊያስከትልበት ይችላል። (ምሳሌ 10:14፤ 18:7) ሰዎች ከአፋቸው ለሚወጣው ነገር በአምላክ ዘንድ ተጠያቂ ናቸው። (ማቴ 12:36, 37) አንድ ሰው በደንብ ሳያስብበት ቸኩሎ ስእለት ሊሳል ወይም ቃል ሊገባ ይችላል። (መክ 5:4-6) ሌሎችን ይሸነግል ይሆናል፤ ይህም በሰዎቹም ሆነ በራሱ ላይ ጥፋት ያስከትላል። (ምሳሌ 26:28) በተለይ ክፉ ሰው አብሮን ሲኖር አፋችንን መጠበቃችን ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም አምላክ በጥበቡ ከሚመራን ጎዳና በትንሹም ቢሆን የራቀ ነገር መናገር በአምላክ ስም ላይ ነቀፋ ሊያስከትል ከዚያም አልፎ ሕይወታችንን ሊያሳጣን ይችላል። (መዝ 39:1) ኢየሱስ ምንም ሳያማርር ለአምላክ ፈቃድ በመገዛት ረገድ ግሩም ምሳሌ ነው፤ ክፉ ጠላቶቹንም ቢሆን አልተሳደበም።—ኢሳ 53:7፤ ሥራ 8:32፤ 1ጴጥ 2:23
ክርስቲያኖች ፍጽምና ስለሚጎድላቸው ምንጊዜም ንቁ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤ በመሆኑም ልባቸውን መጠበቅ አለባቸው። ኢየሱስ ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፉ የሚገባው ነገር ሳይሆን ከአፉ የሚወጣው ነገር እንደሆነ ገልጿል፤ ምክንያቱም “አንደበት የሚናገረው በልብ ውስጥ የሞላውን ነው።” (ማቴ 12:34፤ 15:11) በመሆኑም ሳናስብ ይኸውም ውጤቱን ሳናመዛዝን ላለመናገር ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። ከአምላክ ቃል የተማርናቸውን ነገሮች ተግባራዊ ለማድረግ አእምሯችንን መጠቀማችን በዚህ ረገድ ይረዳናል።—ምሳሌ 13:3፤ 21:23