የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች—ጥቅምት 2016
ጥቅምት 2016
it-2 180
እውቀት
የእውቀት ምንጭ። ይሖዋ የእውቀት ምንጭ ነው። ሕይወት የተገኘው ከእሱ እንደሆነ ግልጽ ነው፤ አንድ ሰው ምንም ዓይነት እውቀት ሊያገኝ የሚችለው ሕይወት ካለው ነው። (መዝ 36:9፤ ሥራ 17:25, 28) ከዚህም በላይ ሁሉንም ነገሮች የፈጠረው አምላክ በመሆኑ የሰው ልጆች እውቀት የሚያገኙት የአምላክን የእጅ ሥራዎች በማጥናት ነው። (ራእይ 4:11፤ መዝ 19:1, 2) በተጨማሪም አምላክ ሰዎች ስለ መለኮታዊ ፈቃድና ዓላማ እንዲያውቁ ቃሉን በመንፈስ መሪነት አጽፏል። (2ጢሞ 3:16, 17) በመሆኑም የእውነተኛ እውቀት ሁሉ ምንጭ ይሖዋ ነው፤ ይህን እውቀት የሚፈልግ ሰው አምላክን መፍራት ይኖርበታል፤ ይህም የእሱን ሞገስ የሚያሳጡ ነገሮችን ከማድረግ እንዲቆጠብ ያደርገዋል። እንዲህ ያለው ፍርሃት የእውቀት መጀመሪያ ነው። (ምሳሌ 1:7) አንድ ሰው አምላካዊ ፍርሃት ካለው ትክክለኛ እውቀት ማግኘት ይችላል፤ በሌላ በኩል ግን አምላክን የማይቀበሉ ሰዎች በሚያዩት ነገር ላይ ተመሥርተው የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ይደርሳሉ።
it-2 818 አን. 4
በትር
የወላጆች ሥልጣን። “በትር” ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ያላቸውን ሥልጣን ለማመልከትም ተሠርቶበታል። የምሳሌ መጽሐፍ ወላጆች ስላላቸው እንዲህ ያለ ሥልጣን በተደጋጋሚ ይናገራል፤ በትር የሚለው ቃል ቅጣት ለመስጠት የሚያገለግለውን በትርን ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ተግሣጽና ቅጣት ያመለክታል። ወላጆች የተሰጣቸውን ይህን በትር እንዲጠቀሙበት ማለትም ልጃቸውን እንዲመሩ ይሖዋ ይጠብቅባቸዋል። አንድ ወላጅ ይህን አለማድረጉ ልጁን ለውድቀትና ለሞት የሚዳርገው ከመሆኑም ሌላ በራሱ ላይ ውርደት ያመጣል። እንዲሁም የይሖዋን ሞገስ ያሳጣዋል። (ምሳሌ 10:1፤ 15:20፤ 17:25፤ 19:13) “ሞኝነት በልጅ ልብ ውስጥ ታስሯል፤ የተግሣጽ በትር ግን ከእሱ ያርቀዋል።” “ልጅን ከመገሠጽ ወደኋላ አትበል። በበትር ብትመታው አይሞትም። ከመቃብር ታድነው ዘንድ በበትር ምታው።” (ምሳሌ 22:15፤ 23:13, 14) እንዲያውም “ልጁን በበትር ከመምታት ወደኋላ የሚል ይጠላዋል፤ የሚወደው ግን ተግቶ ይገሥጸዋል።”—ምሳሌ 13:24፤ 19:18፤ 29:15፤ 1ሳሙ 2:27-36