የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች—ኅዳር 2016
ኅዳር 2016
it-2 1183
ሚስት
የጥሩ ሚስት መገለጫዎች። ምሳሌ 31 አንዲት ታማኝ ሚስት ስለምታገኘው ደስታና ስለምታከናውናቸው የተለያዩ ነገሮች ይዘረዝራል። እንዲህ ያለች ሚስት ለባሏ ከዛጎል ይበልጥ ውድ እንደሆነች ተገልጿል። ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል። እዚህ ላይ የተገለጸችው ሚስት ታታሪ ናት፤ ትሸምናለች፣ ለቤተሰቡ ልብስ ትሠራለች፣ እንዲሁም ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ነገር ትገዛለች፣ በወይን እርሻ ውስጥ ትሠራለች፣ ለቤቷ ሠራተኞች ሥራ ታከፋፍላለች፣ የተቸገረ ሰው ትረዳለች፣ ቤተሰቧ አምሮበት እንዲታይ ታደርጋለች፣ ለቤተሰቡ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ ትሠራለች፣ ቤተሰቧን ወደፊት ለሚያጋጥመው ድንገተኛ ሁኔታ ታዘጋጃለች፣ በጥበብና በደግነት ትናገራለች፣ ይሖዋን የምትፈራና ትጉ ሠራተኛ ስለሆነች ባሏና ልጆቿ ያወድሷታል፣ በዚህም የተነሳ ባሏና ቤተሰቧ በአገሩ የተከበሩ ይሆናሉ። በእርግጥም ጥሩ ሚስት ያገኘ ጥሩ ነገር አግኝቷል፤ የይሖዋንም ሞገስ ያገኛል።—ምሳሌ 18:22