መዝሙር 99
አዲሱን የምድር ንጉሥ አወድሱ
በወረቀት የሚታተመው
(ራእይ 7:9)
1. ከብሔራት የተውጣጡ እጅግ ብዙ ሕዝቦችን፣
በመሰብሰብ ላይ ናቸው ክርስቶስና ቅቡዓን።
በመሰብሰብ ላይ ናቸው ክርስቶስና ቅቡዓን።
የአምላክ መንግሥት ተወልዷል፤
በቅርቡ ምድርን ይገዛል።
ይህ ተስፋ ነው ታላቅ ስጦታ፤
ያስገኛል መጽናኛ ደስታ።
(አዝማች)
ይወደስ ይሖዋ፤
ይወደስ ኢየሱስ፤
በቤዛው ነፃ ስላወጡን።
ምድር ላይ ዘላለም
እ’ኖራለን አምላክን እያወደስን።
2. ክርስቶስ በመግዛት ላይ ነው፤
እንግለጽ ደስታችንን።
ያምላክን ፈቃድ ያደርጋል፤
ያድነናል ይህ መስፍን።
ይታየናል ደስታው ካሁን፣
ሽብር ሲጠፋ ከምድር፣
ሙታን ሲወጡ ከመቃብር፣
ሐሴት ያደርጋል የሰው ዘር!
(አዝማች)
ይወደስ ይሖዋ፤
ይወደስ ኢየሱስ፤
በቤዛው ነፃ ስላወጡን።
ምድር ላይ ዘላለም
እ’ኖራለን አምላክን እያወደስን።