ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢሳይያስ 11-16
ምድር በይሖዋ እውቀት ትሞላለች
ይህ ትንቢት በእስራኤላውያን ላይ የተፈጸመው እንዴት ነው?
እስራኤላውያን ከባቢሎን ግዞት ወደ አገራቸው ሲመለሱም ሆነ በምድሪቱ ሲኖሩ የዱር አራዊትንና እንደ አውሬ ያሉ ሰዎችን የሚፈሩበት ምክንያት አልነበራቸውም። —ዕዝራ 8:21, 22
ይህ ትንቢት በዘመናችን እየተፈጸመ ያለው እንዴት ነው?
የይሖዋ እውቀት የሰዎችን ባሕርይ ይለውጣል። ዓመፀኛ የነበሩ ሰዎች ተለውጠው ሰላማዊ ሆነዋል። የአምላክ እውቀት በዓለም ዙሪያ መንፈሳዊ ገነት እንዲፈጠር አስችሏል
ይህ ትንቢት ወደፊት የሚፈጸመው እንዴት ነው?
አምላክ መጀመሪያ በነበረው ዓላማ መሠረት መላዋ ምድር ምንም የሚያስፈራ ነገር ወደሌለባት ሰላማዊ ገነት ትለወጣለች። ሰዎችም ሆኑ እንስሳት በማንም ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አያደርሱም