መዝሙር 134
ልጆች ከአምላክ በአደራ የተሰጡ ናቸው
በወረቀት የሚታተመው
1. ወንድ አባት ሲሆን ልጅ ሲያገኝ፣
ሴትም ወልዳ ስታቅፍ የራሷን ልጅ፣
አይዘንጉ የነሱ ብቻ
እንዳልሆነ ይህ ስጦታ።
ይህ አደራ ከይሖዋ ነው፤
ሕይወትና ፍቅር ከሚሰጠው።
እንዲመሯቸው በትክክል፣
ለወላጆች መመሪያ ሰጥቷል።
(አዝማች)
አደራ ነው ይህ ኃላፊነት፤
በ’ጃችሁ ነው ክቡር ሕይወት።
ታላቅ መብትም አግኝታችኋል፤
ልጁን ምሩት በአምላክ ቃል።
2. በልባችሁ ውስጥ አኑሩ፣
ት’ዛዛቱን አንድም ሳታስቀሩ።
ከዚያም አውሩ ለልጆቻችሁ፤
ይህን ማድረግ ነው ድርሻችሁ።
ስትጓዙ፣ አረፍ ስትሉ፣
ስትነሱም ቃሉን አስተምሯቸው።
ለወደፊቱ አስታውሰውት፣
ይባረኩ ታማኞች ሆነው።
(አዝማች)
አደራ ነው ይህ ኃላፊነት፤
በ’ጃችሁ ነው ክቡር ሕይወት።
ታላቅ መብትም አግኝታችኋል፤
ልጁን ምሩት በአምላክ ቃል።
(በተጨማሪም ዘዳ. 6:6, 7ን፣ ኤፌ. 6:4ን እና 1 ጢሞ. 4:16ን ተመልከት።)