ክርስቲያናዊ ሕይወት
‘ሥጋህን የሚወጋ እሾህ’ ቢኖርም በይሖዋ አገልግሎት ስኬታማ መሆን ትችላለህ!
ለመቋቋም በሚያስቸግረው በዚህ የመጨረሻ ዘመን የሚኖሩ የአምላክ አገልጋዮች በሙሉ እንደ እሾህ ያሉ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። (2ጢሞ 3:1) በይሖዋ መታመንና እነዚህን ችግሮች መቋቋም የምንችለው እንዴት ነው? ታሊታ አልናሺ እና ወላጆቿ ይህን ማድረግ የቻሉት እንዴት እንደሆነ ለማወቅ “የዓይነ ስውራን ዓይን ይገለጣል” የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
የታሊታ ‘የሥጋ መውጊያ እሾህ’ ምንድን ነው?
ታሊታ እና ወላጆቿ አዎንታዊ አመለካከት እንዲይዙ የረዷቸው የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋዎች ናቸው?
ታሊታ ቀዶ ሕክምና ካደረገች ብዙም ሳይቆይ ወላጆቿ በይሖዋ እንደታመኑ ያሳዩት እንዴት ነው?
የታሊታ ወላጆች፣ ድርጅቱ ባደረጋቸው ዝግጅቶች ጥሩ አድርገው በመጠቀም ታሊታ አምላክን እንድትወድ የረዷት እንዴት ነው?
ታሊታ ‘ሥጋዋን የሚወጋ እሾህ’ እያለም መንፈሳዊ እድገት እያደረገች መሆኗን ያሳየችው እንዴት ነው?
የታሊታ ምሳሌ ያበረታታህ እንዴት ነው?