ክርስቲያናዊ ሕይወት
ድርቅ በሚከሰትበት ዓመት ምን ታደርጉ ይሆን?
እምነትና የመተማመን ስሜት በጥብቅ የተቆራኙ ናቸው። ለምሳሌ ያህል፣ በይሖዋ ላይ ጠንካራ እምነት ካለን እሱ እንደሚጠብቀን እና እንደሚንከባከበን እንተማመናለን። (መዝ 23:1, 4፤ 78:22) ሰይጣን የሚሰነዝራቸው ጥቃቶች ወደ ሥርዓቱ መጨረሻ ይበልጥ በተቃረብን መጠን እየጨመሩ እንደሚሄዱ መጠበቅ እንችላለን። (ራእይ 12:12) ታዲያ ምን ሊረዳን ይችላል?
ድርቅ በሚከሰትበት ዓመት ምን ታደርጉ ይሆን? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
በኤርምያስ 17:8 ላይ ከተጠቀሰው “ዛፍ” ጋር የምንመሳሰለው በምን መንገድ ነው?
አንደኛው ‘የሙቀት’ ዓይነት ምንድን ነው?
‘ዛፉ’ ምን ሊደርስበት ይችላል? ለምንስ?
ሰይጣን ሊያጠፋ የሚፈልገው ምናችንን ነው?
ልምድ ካላቸው የአውሮፕላን ተጓዦች ጋር የምንመሳሰለው በምን መንገድ ነው?
ምንጊዜም በታማኝና ልባም ባሪያ መታመን ያለብን ለምንድን ነው? እምነታችን የሚፈተነው እንዴት ነው?
ሰዎች ቢያሾፉብንም ምንጊዜም በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች መታመን ያለብን ለምንድን ነው?