የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 5 ገጽ 8
  • ጥርት ያለ ንባብ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥርት ያለ ንባብ
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥርት ያለ ንባብ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ለማንበብ ትጋ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ማንበብና ያነበቡትን ማስታወስ የሚቻልበት መንገድ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • ንባብህን ልታሻሽል ትችላለህ
    ንቁ!—1993
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 5 ገጽ 8

ጥናት 5

ጥርት ያለ ንባብ

ጥቅስ

1 ጢሞቴዎስ 4:13

ፍሬ ሐሳብ፦ በጽሑፉ ላይ የሰፈረውን ነገር ምንም ሳትጨምርና ሳትቀንስ አንብብ።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • በሚገባ ተዘጋጅ። ጽሑፉ የተዘጋጀበትን ዓላማ ለመረዳት ጥረት አድርግ። በምታነብበት ጊዜ ቃላትን በተናጠል ከማንበብ ይልቅ የተወሰኑ ቃላትን አንድ ላይ ለማንበብ ሞክር። ቃላትንና ፊደላትን ላለመግደፍ ወይም አንዱን ቃል በሌላ ተክተህ ላለማንበብ ጥንቃቄ አድርግ። ሁሉንም ሥርዓተ ነጥቦች (ለምሳሌ ጥያቄ ምልክት፣ ነጠላ ሰረዝ ወይም ድርብ ሰረዝ) አስተውል።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    በምታነብበት ጊዜ አንድ ጓደኛህ እንዲከታተልህና በተሳሳተ መንገድ ስታነብ እንዲጠቁምህ አድርግ።

  • እያንዳንዱን ቃል በትክክል ጥራ። አንድን ቃል እንዴት መጥራት እንዳለብህ ካላወቅክ መዝገበ ቃላት ተመልከት፣ በድምፅ የተቀዱ ጽሑፎችን አዳምጥ ወይም ጥሩ አንባቢ የሆነ ሰው እንዲረዳህ ጠይቅ።

  • ጥርት አድርገህ ተናገር። ቀና ብለህና አፍህን በደንብ ከፍተህ ቃላትን ጥርት ባለ መንገድ ለማንበብ ጥረት አድርግ። ቃላትን ሳትውጥ ወይም አንድ ላይ ሳትጨፈልቅ ግልጽ ሆኖ በሚሰማ መንገድ አንብብ።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    ቃላትን ጥርት አድርገህ ለመጥራት ስትጨነቅ ንባብህ ለዛውን እንዳያጣ መጠንቀቅ ያስፈልግሃል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ