የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 2 ገጽ 5
  • በጭውውት መልክ መናገር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በጭውውት መልክ መናገር
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጋለ ስሜት መናገር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • የራስን ተፈጥሮአዊ አነጋገር መጠቀም
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • በእርግጠኝነት መናገር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ወዳጃዊ ስሜትና አሳቢነት ማሳየት
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 2 ገጽ 5

ጥናት 2

በጭውውት መልክ መናገር

ጥቅስ

2 ቆሮንቶስ 2:17

ፍሬ ሐሳብ፦ የራስህን ተፈጥሮአዊ አነጋገር ተጠቅመህ ከልብ በመነጨ ስሜት ተናገር፤ አነጋገርህ ስለ ርዕሰ ጉዳዩም ሆነ ስለ አድማጮችህ ምን እንደሚሰማህ የሚያሳይ ይሁን።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ወደ ይሖዋ ጸልይ እንዲሁም በሚገባ ተዘጋጅ። በራስህ ላይ ሳይሆን በመልእክቱ ላይ ለማተኮር እንዲረዳህ ወደ ይሖዋ ጸልይ። የምታስተላልፋቸው ዋና ዋና ነጥቦች ቁልጭ ብለው ይታዩህ። በጽሑፉ ላይ የሰፈሩትን ሐሳቦች ቃል በቃል ከመድገም ይልቅ ነጥቡን በራስህ አባባል ግለጸው።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከሌላ ጽሑፍ ላይ የምታነብ ከሆነ ጥርት ባለና ለዛ ባለው መንገድ ማንበብ እንድትችል በደንብ ተለማመድ። ሌሎች ሰዎች የተናገሩትን ሐሳብ የምታነብ ከሆነ ደግሞ ስሜቱን በሚያንጸባርቅ መንገድ ለማንበብ ጥረት አድርግ፤ ሆኖም አነባበብህ ከልክ በላይ የተጋነነ እንዳይሆን ተጠንቀቅ።

  • ከልብ በመነጨ ስሜት ተናገር። መልእክቱ ለአድማጮችህ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ቆም ብለህ አስብ። በእነሱ ላይ ትኩረት አድርግ። እንዲህ ካደረግክ አቋቋምህ፣ አካላዊ መግለጫዎችህ እንዲሁም በፊትህ ላይ የሚነበበው ስሜት ከልብህ እንደምትናገር የሚያሳይና ወዳጃዊ መንፈስ የሚንጸባረቅበት ይሆናል።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    የራስህን ተፈጥሮአዊ አነጋገር መጠቀም ሲባል ግን ግዴለሽነት በሚንጸባረቅበት መንገድ መናገር ማለት አይደለም። አድማጮች ለመልእክቱ አክብሮት እንዲኖራቸው፣ ጥርት ባለና የቋንቋውን ሰዋስው በጠበቀ መንገድ ለመናገር ጥረት አድርግ።

  • አድማጮችህን እያየህ ተናገር። በአካባቢያችሁ እንደ ነውር የማይታይ ከሆነ አድማጮችህን ፊት ለፊት እያየህ ተናገር። ንግግር በምታቀርብበት ጊዜ አድማጮችህን በጥቅሉ ገረፍ አድርገህ ከማየት ይልቅ የተለያዩ ግለሰቦችን በየተራ እያየህ ለመናገር ጥረት አድርግ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ