ክርስቲያናዊ ሕይወት
የምታምንበትን ነገር ማስረዳት ትችላለህ?
አንድ ሰው ‘አምላክ ሁሉንም ነገር እንደፈጠረ የምታምነው ለምንድን ነው?’ ቢልህ ምን መልስ ትሰጣለህ? በልበ ሙሉነት መልስ ለመስጠት ሁለት ነገሮች ማድረግ ይኖርብሃል፦ በመጀመሪያ፣ ሁሉንም ነገር የፈጠረው አምላክ እንደሆነ ለራስህ ማረጋገጥ ያስፈልግሃል። (ሮም 12:1, 2) ከዚያም የምታምንበትን ነገር ለሌላ ሰው ማስረዳት የምትችለው እንዴት እንደሆነ ማሰብ ይኖርብሃል።—ምሳሌ 15:28
አንዳንድ ሰዎች በፍጥረት እንዲያምኑ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ አንዲት የአጥንት ቀዶ ሕክምና ባለሙያ ስለምታምንበት ነገር ምን ትላለች? እና አንድ የሥነ እንስሳት ተመራማሪ ስለሚያምንበት ነገር ምን ይላል? የሚሉትን ቪዲዮዎች ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ኢሬን ሆፍ ሎራንሶ ከዝግመተ ለውጥ ይልቅ በፍጥረት ማመን የጀመረችው ለምንድን ነው?
ያሮስላቭ ዶቫኒች ከዝግመተ ለውጥ ይልቅ በፍጥረት ማመን የጀመረው ለምንድን ነው?
በፍጥረት የምታምነው ለምን እንደሆነ ለሌሎች ማስረዳት የምትችለው እንዴት ነው?
ሁሉንም ነገር የፈጠረው አምላክ እንደሆነ ለራስህ ለማረጋገጥም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ለማስረዳት የሚረዱህ በቋንቋህ የተዘጋጁ ምን ጽሑፎች አሉ?