ጥናት 1
ጥሩ መግቢያ
የሐዋርያት ሥራ 17:22
ፍሬ ሐሳብ፦ መግቢያህ አድማጮች ጉጉት እንዲያድርባቸው የሚያደርግ፣ ርዕሰ ጉዳዩ ምን እንደሆነ የሚገልጽ እንዲሁም ለትምህርቱ ትኩረት ሊሰጡት የሚገባው ለምን እንደሆነ የሚጠቁም መሆን አለበት።
ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
ጉጉት እንዲያድርባቸው አድርግ። የአድማጮችህን ትኩረት ሊስብ የሚችል ጥያቄ፣ እውነተኛ ታሪክ፣ የዜና ዘገባ ወይም ሌላ ነገር ጥቀስ።
ርዕሰ ጉዳዩ ምን እንደሆነ ጠቁም። መግቢያህ ርዕሰ ጉዳዩንና ዓላማውን ለአድማጮችህ ግልጽ የሚያደርግ መሆን አለበት።
ትምህርቱ እንዴት እንደሚጠቅማቸው ግለጽ። አድማጮችህን ሊጠቅሙ የሚችሉ ነገሮችን ከግምት በማስገባት መግቢያህ በዚያ ላይ ያተኮረ እንዲሆን አድርግ። አድማጮችህ የምትናገረው ነገር በግለሰብ ደረጃ እንዴት እንደሚጠቅማቸው ግልጽ ሊሆንላቸው ይገባል።