የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 3 ገጽ 6
  • ጥያቄዎችን መጠቀም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥያቄዎችን መጠቀም
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥያቄዎችን በጥሩ ሁኔታ መጠቀም
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ ማስተዋወቅ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • የአድማጮችን ልብ ለመንካት መጣር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 3 ገጽ 6

ጥናት 3

ጥያቄዎችን መጠቀም

ጥቅስ

ማቴዎስ 16:13-16

ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህ ለመልእክቱ ጉጉት እንዲያድርባቸውና ተመስጠው እንዲከታተሉህ ለማድረግ፣ ነጥቡን አሳማኝ በሆነ መንገድ ለማስረዳት እንዲሁም ዋና ዋና ነጥቦችን ለማጉላት ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ተጠቀም።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • አድማጮችህ ጉጉት እንዲያድርባቸውና ተመስጠው እንዲከታተሉህ አድርግ። አድማጮች ስለ ትምህርቱ ቆም ብለው እንዲያስቡ ወይም መልሱን ለማወቅ እንዲጓጉ የሚያደርጉ ጥያቄዎችን ተጠቀም።

  • ነጥቡን አሳማኝ በሆነ መንገድ አስረዳ። አድማጮች ትክክለኛው መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ የሚረዱ ጥያቄዎችን በማንሳት ትምህርቱን አሳማኝና ግልጽ በሆነ መንገድ አቅርብ።

  • ዋና ዋና ነጥቦችን አጉላ። የማወቅ ፍላጎት የሚቀሰቅሱ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ቁልፍ ነጥቦችን ማስተዋወቅ ትችላለህ። አንድ አስፈላጊ ነጥብ ካብራራህ በኋላ ወይም ደግሞ ንግግርህን ስትደመድም የክለሳ ጥያቄዎችን ተጠቀም።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    አንድ ጥቅስ ካነበብክ በኋላ በጥቅሱ ላይ የሚገኘውን ዋና ነጥብ ለማጉላት ጥያቄዎችን መጠቀም ትችላለህ።

ለአገልግሎት

የምታነጋግረው ሰው ስለ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ያለውን አመለካከት እንዲገልጽ ጥያቄ አቅርብለት። የሚሰጥህን መልስ በጥሞና አዳምጥ። ምን ዓይነት ጥያቄዎችን ማንሳት እንዲሁም መቼ መጠየቅ እንዳለብህ ለማወቅ አስተዋይ መሆን ያስፈልግሃል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ