የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 19 ገጽ 22
  • የአድማጮችን ልብ ለመንካት መጣር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአድማጮችን ልብ ለመንካት መጣር
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጋለ ስሜት መናገር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ልብ ለመንካት መጣር
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • አዎንታዊና የሚያበረታታ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 19 ገጽ 22

ጥናት 19

የአድማጮችን ልብ ለመንካት መጣር

ጥቅስ

ምሳሌ 3:1

ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህ የትምህርቱን ጠቀሜታ እንዲገነዘቡና የተማሩትን በተግባር ለማዋል እንዲነሳሱ እርዳቸው።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • አድማጮችህ ራሳቸውን እንዲመረምሩ እርዳቸው። አንዳንድ ጥያቄዎችን በማንሳት፣ አድማጮች ስለ ጉዳዩ ያላቸውን አመለካከት እንዲፈትሹ ለመርዳት ጥረት አድርግ።

  • በጥሩ የልብ ዝንባሌ ተነሳስተው እርምጃ እንዲወስዱ አበረታታቸው። አድማጮችህ መልካም ነገሮችን ለማድረግ የሚነሳሱበትን ምክንያት እንዲመረምሩ እርዳቸው። ጥሩ የልብ ዝንባሌ እንዲያዳብሩ አበረታታቸው፤ ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ የሚያነሳሳቸው ለይሖዋ፣ ለሰዎች እንዲሁም ለመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ያላቸው ፍቅር መሆን አለበት። አድማጮችህ መመሪያ እየሰጠሃቸው እንዳለ እንዲሰማቸው ከማድረግ ይልቅ የትምህርቱን ጥቅም እንዲያስተውሉ እርዳቸው። ንግግርህ የሚያበረታታና ለተግባር የሚያነሳሳ እንጂ አድማጮችህን የሚያሸማቅቅ ሊሆን አይገባም።

  • ሰዎች በይሖዋ ላይ እንዲያተኩሩ አድርግ። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች፣ መሠረታዊ ሥርዓቶችና ትእዛዞች የአምላክን ባሕርያት እንዲሁም ለእኛ ያለውን ፍቅር የሚያንጸባርቁት እንዴት እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ። አድማጮችህ የይሖዋን አመለካከት ከግምት እንዲያስገቡና እሱን ለማስደሰት እንዲጥሩ አበረታታቸው።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    ሰዎችን ወደ ራሱ የሚስበው ይሖዋ እንደሆነ አስታውስ። በመሆኑም በቃሉ ተጠቅመህ አድማጮችህን ለተግባር ለማነሳሳት ጥረት አድርግ።

ለአገልግሎት

የምታነጋግረው ሰው የሚያምንበትን ነገር ለማወቅ፣ አመቺ በሚሆንበት ጊዜ ጥያቄዎችን ተጠቀም። እውነተኛ ስሜቱን ለመረዳት እንድትችል ፊቱ ላይ የሚነበበውን ነገር እንዲሁም የድምፁን ቃና ልብ ብለህ ተከታተል። ሆኖም ትዕግሥት ይኑርህ። የምታነጋግረው ሰው የልቡን አውጥቶ የሚነግርህ በአንተ ላይ እምነት እንዲጥል ማድረግ ስትችል ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ