መዝሙር 94
ለአምላክ ቃል አመስጋኝ መሆን
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ አባት ሆይ፣ ደርሶናል ቃልህ፤
ማመስገን እንሻለን ለስጦታህ።
በመንፈስህ በመምራት
አ’ጻፍክ ሐሳብህን፤
ቃልህ ብርሃን ሆነን፤ እውነትን ተማርን።
2. ወደ ልብ ይዘልቃል፤ ቃልህ አለው ኃይል፤
መንፈስንና ነፍስን ይለያያል።
እንከን የለውም ሕግህ፤
ፍጹም ነው ት’ዛዝህ፤
አስተማማኝ ናቸው መመሪያዎችህ።
3. በሰዎች ተጠቅመህ ባ’ጻፍከው ቃልህ
ልባችን ተነካ፤ አንተን አወቅንህ።
ቃልህን ሰጥተኸናል፤
ይድረስህ ምስጋና፤
እምነታችን ይደግ፣ ይሁን ጠንካራ።
(በተጨማሪም መዝ. 19:9፤ 119:16, 162ን፣ 2 ጢሞ. 3:16ን፣ ያዕ. 5:17ን እና 2 ጴጥ. 1:21ን ተመልከት።)