የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 8/10 ገጽ 31
  • ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ የሚወያይበት
  • ንቁ!—2010
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይህን ሥራ ይሠሩ የነበሩት እነማን ነበሩ?
  • ስለ ሐዋርያው እንድርያስ ምን የምታውቀው ነገር አለ?
  • ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
  • ከዚህ እትም
  • በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2010
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2010
  • መልስህ ምንድን ነው?
    ንቁ!—2008
  • መልስህ ምንድን ነው?
    ንቁ!—2008
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2010
g 8/10 ገጽ 31

ቤተሰብ የሚወያይበት

ይህን ሥራ ይሠሩ የነበሩት እነማን ነበሩ?

1. የዘብዴዎስ ልጆችና የኢየሱስ ሐዋርያት የነበሩት ሁለቱ ዓሣ አጥማጆች እነማን ናቸው?

መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።

ፍንጭ፦ ማቴዎስ 4:21, 22ን አንብብ።

․․․․․

2. ዓሣ አጥማጆች የነበሩ ሌሎች ሁለት ሐዋርያት ማን ይባላሉ?

ፍንጭ፦ ማቴዎስ 4:18ን አንብብ።

․․․․․

ለውይይት፦

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ‘ሰዎች አጥማጆች’ እንደሚሆኑ የተናገረው ለምንድን ነው? (ማቴዎስ 4:19) ዓሣ ማጥመድና ሰው ማጥመድ ምን ተመሳሳይነትና ልዩነት ያላቸው ይመስልሃል?

ስለ ሐዋርያው እንድርያስ ምን የምታውቀው ነገር አለ?

3. እንድርያስ የኢየሱስ ተከታይ ከመሆኑ በፊት የማን ደቀ መዝሙር ነበር?

ፍንጭ፦ ማርቆስ 1:4ን እና ዮሐንስ 1:35-40ን አንብብ።

․․․․․

4. እንድርያስ ስለ ኢየሱስ የተነጋገረው ከማን ጋር ነበር? ውጤቱስ ምን ነበር?

ፍንጭ፦ ዮሐንስ 1:40-42ን አንብብ።

․․․․․

ለውይይት፦

ስለ ኢየሱስ የምታውቀውን ነገር ለዘመዶችህ መንገር ጥሩ የሆነው ለምንድን ነው? ሆኖም አንዳንድ ዘመዶችህ ምን ዓይነት ምላሽ ሊሰጡ ይችላሉ?

ፍንጭ፦ ማቴዎስ 10:32-37ን አንብብ።

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 3 አስተዋይ ወይም ብልህ ሰው ምን ያስተውላል? ምሳሌ 14:․․․

ገጽ 8 አምላክ ለራሱ ምን ስም አውጥቷል? ዘፀአት 6:․․․

ገጽ 20 ኃጢአት የሠሩት መላእክት ምን ሆነዋል? ይሁዳ․․․

ገጽ 26 “ቍጣን ማነሣሣት” ምን ያስከትላል? ምሳሌ 30:․․․

● መልሶቹ በገጽ 11 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. ያዕቆብና ዮሐንስ።

2. ጴጥሮስና እንድርያስ።

3. የአጥማቂው ዮሐንስ።

4. ከወንድሙ ከጴጥሮስ ጋር፤ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ሆነ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ