የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 1/12 ገጽ 20
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—2012
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቀሳውስት ለፖለቲካ ሥልጣን እንዲወዳደሩ ተፈቀደላቸው
  • አዳዲስ የሕግ ጥያቄዎች ተነሱ
  • ከዓለም አካባቢ
    ንቁ!—2011
  • ማሽኮርመም ምንም ጉዳት የለውም?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ከዓለም አካባቢ
    ንቁ!—2010
  • በመጨረሻ እውነተኛ ነፃነት አገኘሁ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 1/12 ገጽ 20

ከዓለም አካባቢ

ጀርመን ውስጥ ጥናት ከተካሄደባቸው ጎልማሶች መካከል 76.3 በመቶ የሚሆኑት ማሽኮርመም “ፈጽሞ ጉዳት እንደሌለው” እንዲሁም የሚያሽኮረምመው ሰው ይህን የሚያደርገው “የግድ የፍቅር ጓደኝነት የመጀመር ፍላጎት ኖሮት ላይሆን” እንደሚችል ገልጸዋል። ጥናቱ ከተካሄደባቸው መካከል ግማሽ ገደማ የሚሆኑት፣ ባለትዳሮች የማያውቁትን ሰው ቢያሽኮረምሙ ምንም ችግር እንደሌለው ተናግረዋል።​—አፖቴከን ኡምሻው፣ ጀርመን

አንድ በአገር አቀፍ ደረጃ የተካሄደ ጥናት እንዳሳየው ከሆነ 48 በመቶ የሚያህሉ ሩሲያውያን የሽብርተኝነት ጥቃት “ሁሉም ሰው የሚጠብቀው” እና “የዕለታዊ ኑሮ ክፍል” እንደሆነ ያምናሉ።​—ከመርሳንት፣ ሩሲያ

በቅርቡ የሜክሲኮ ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች የድንበር ጠባቂዎችን አታለው ለማለፍ ሲሉ ታይቶም ተሰምቶም የማያውቅ ዘዴ በመጠቀም “ከመካከለኛው ዘመን የውጊያ ከበባ ጋር የሚመሳሰል ዓይን ያወጣ ድርጊት” ፈጽመዋል። እነዚህ ሰዎች በአንድ የመኪና ተሳቢ ላይ የተጫነ “ትልቅ ማስወንጨፊያ” በመጠቀም የዩናይትድ ስቴትስን የድንበር አጥር አሻግረው “ዕፆችን ወደ ሰሜን አቅጣጫ ለመወርወር” ሞክረዋል።​—ሮይተርስ ዜና አገልግሎት፣ ዩናይትድ ስቴትስ

ኒው ዮርክ ሲቲ ውስጥ “ከአምስት ፅንሶች ውስጥ ሁለቱ” በውርጃ ይቋረጣሉ። ይህ ቁጥር “ከአሥር ዓመታት በሚበልጥ ጊዜ ውስጥ እምብዛም ለውጥ አላሳየም።”​—ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

የተባይ ተቆጣጣሪዎች በማዕከላዊ ለንደን እየተገነባ ባለ አንድ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ 72ኛ ፎቅ ላይ አንድ ቀበሮ እንዲይዙ ጥሪ በደረሳቸው ጊዜ ተገርመው ነበር። “ከግንባታ ሠራተኞቹ የተራረፈውን ምግብ ሲበላ የቆየው” ይህ እንስሳ ከተያዘ በኋላ ብዙም ባልራቀ አካባቢ ተለቋል።​—ዘ ቴሌግራፍ፣ ለንደን

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቀሳውስት ለፖለቲካ ሥልጣን እንዲወዳደሩ ተፈቀደላቸው

“የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመከፋፈልና ከሌሎች ቀጥተኛ ጥቃቶች ለመከላከል፣ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ቀሳውስቱ ለፖለቲካ ሥልጣን እንዲወዳደሩ ፈቃድ ሰጠ” በማለት ሪያ ኖቮስቲ የተሰኘው የዜና ወኪል ዘግቧል። ጳጳሳቱ በሰጡት መግለጫ መሠረት ይህ የሚሆነው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ “መከፋፈል ለመፍጠር የሚሞክሩትን ጨምሮ በምርጫ ያገኙትን ሥልጣን ተጠቅመው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም የሚጥሩ ሌሎች የእምነት ድርጅቶች የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ መቋቋም” አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ነው።

አዳዲስ የሕግ ጥያቄዎች ተነሱ

በሳይንሳዊ ልብ ወለዶች ውስጥ ካልሆነ በስተቀር በእውን ይሆናል ተብሎ የማይታሰበው፣ በሕክምና ዘዴዎች ተጠቅሞ ልጅ የማግኘቱ ጉዳይ አዳዲስ የሕግ ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው። “ለወራት ወይም ለዓመታት ተቀምጦ የቆየን የወንድ ዘር ፈሳሽ ወይም ጽንስ በመጠቀም የሚወለዱ ሕፃናት ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ ነው” በማለት ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል ተናግሯል። “አንዳንድ ጊዜ ልጁ ሲወለድ አንደኛው ወላጅ (በአብዛኛው አባትየው ነው) በሕይወት አይኖርም።” በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የማኅበራዊ ዋስትና ተቋም ለአንዳንድ ወላጅ አልባ ሕፃናት በየወሩ ገንዘብ ይሰጣል። ይሁን እንጂ ልጁ የተጸነሰው አንዱ ወላጅ ከሞተ በኋላ በሚሆንበት ጊዜ እንዲህ ዓይነቱ ክፍያ መፈጸም አለበት ወይስ የለበትም ከሚለው ጉዳይ ጋር በተያያዘ በየግዛቶቹ ያለው ሕግ ይለያያል። “ሕጉ ከቴክኖሎጂ እኩል መራመድ አልቻለም” በማለት የሚኒሶታ ጠበቃ የሆኑት ሶኒ ሚለር ተናግረዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ