የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 2/12 ገጽ 29
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—2012
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወጣት መሪዎች በማሌዥያ
  • ጥንቃቄ የጎደለው የኢንተርኔት አጠቃቀም
  • በኢንተርኔት ጓደኝነት ብመሠርት ምን ችግር አለው?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 2
  • ወጣቶች ችግሩን እንዲቋቋሙ መርዳት
    ንቁ!—2007
  • ኢንተርኔት የሚጠቀሙ ልጆች ወላጆች ማወቅ የሚገባቸው ነገር
    ንቁ!—2008
  • የኢንተርኔት ጓደኞችህ እነማን ናቸው?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 2/12 ገጽ 29

ከዓለም አካባቢ

“ፕሬዚዳንት መሆን አንድ ሰው መጸለይ እንዳለበት እንዲሰማው ያደርጋል።”​—ባራክ ኦባማ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ኦቭ አሜሪካ ፕሬዚዳንት

ከ10 እስከ 24 ዓመት ባለው ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ አርጀንቲናውያን ብሔራዊ ኩራታቸውን በምን መንገድ መግለጽ እንደሚፈልጉ ሲጠየቁ 56 በመቶ የሚሆኑት የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድናቸውን ማሊያ መልበስ እንደሚመርጡ ተናግረዋል።​—ላ ናሲዮን፣ አርጀንቲና

ከአንድ ጥናት የተገኙ ውጤቶች እንደሚያመለክቱት “በመላው ዓለም ለሰዎች ተብሎ ከሚመረተው ምግብ ውስጥ አንድ ሦስተኛ ገደማ የሚሆነው ይበላሻል ወይም ይባክናል፤ ይህም በየዓመቱ 1.3 ቢሊዮን ቶን ይሆናል።”​—የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የግብርና ድርጅት፣ ጣሊያን

“በዛሬው ጊዜ ጦርነትና የጦርነት ወሬ ምድርን ስለሞላት የአባት አገራችን ሠራዊት ወገኖቹንና እንደ ቅዱስ የሚታዩ ነገሮችን በሙሉ ከውጭ ጠላት ለመጠበቅ ምንጊዜም ዝግጁ መሆን ይኖርበታል።”​—ፓትሪያርክ ኪሪል፣ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሪ

በ2010 ለአንድ የጀርመን የመድን ድርጅት ሪፖርት ከተደረጉት የትራፊክ አደጋዎች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያለው አደጋ የደረሰው ከጠዋቱ 1:00 እስከ 2:00 ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። በድርጅቱ ውስጥ በኃላፊነት ቦታ ላይ የሚሠሩ አንድ ግለሰብ እንደገለጹት “አደጋን ለመከላከል ከሚረዱት ቁልፍ ዘዴዎች አንዱ ጠዋት ወደ ሥራ ሲሄዱ ቀደም ብሎ መውጣት ነው።”​—ፕሬሲፖርታል፣ ጀርመን

ወጣት መሪዎች በማሌዥያ

በማሌዥያ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ አንድ ውድድር በቴሌቪዥን የሚሰራጭ ሲሆን ዓላማው ጥሩ ኢማም ወይም የእስልምና ሃይማኖታዊ መሪ መምረጥ ነው። “ኢማም ሙዳ” ወይም “ወጣት መሪ” የሚል ርዕስ ያለው ይህ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የሚቀረጸው በክዋላ ሉምፑር ነው። ከተለያየ የማኅበረሰቡ ክፍል የሚመጡትና ከ18 እስከ 27 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ተወዳዳሪዎች ተራ በተራ እየተሸነፉ ሲሄዱ መጨረሻ ላይ አንድ አሸናፊ ይቀራል። ለአሸናፊው የተዘጋጁት ሽልማቶች ገንዘብንና አዲስ መኪናን የሚያካትቱ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ግለሰቡ ኢማም ሆኖ የማገልገል፣ በሳውዲ አረቢያ ነፃ ትምህርት የመከታተልና የመጓጓዣ ወጪው ተሸፍኖለት ወደ መካ መንፈሳዊ ጉዞ የማድረግ አጋጣሚ ይሰጠዋል። ተወዳዳሪዎች ከአንድ ኢማም የሚጠበቀውን ኃላፊነት ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ በሃይማኖታዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መከራከር እንዲሁም ቁርዓንን በቃላቸው መውጣት የሚችሉ መሆን አለባቸው። የፕሮግራሙ አዘጋጅ፣ ዓላማው ወጣቶችን ወደ እስልምና “መሳብ” እንደሆነ ይናገራሉ።

ጥንቃቄ የጎደለው የኢንተርኔት አጠቃቀም

ማኅበራዊ ድረ ገጾችን የሚጠቀሙ ብዙ ሰዎች የግል ጉዳያቸውን በድረ ገጻቸው ላይ ማስፈራቸው ሊያስከትል የሚችለውን መዘዝ አርቀው አይመለከቱም። ሆኖም በዚህ ረገድ ጥንቃቄ አለማድረግ የኋላ ኋላ ሊያስቆጭ ይችላል። በአውስትራሊያው ሲድኒ ሞርኒንግ ሄራልድ ላይ የተጠቀሱ ቲመቲ ራይት የተባሉ አንድ ርዕሰ መምህር እንዲህ ብለዋል፦ “ዘመናዊው ቴክኖሎጂ ድረ ገጻችሁ ላይ ሳታስቡ የተናገራችሁት ነገር፣ ስለ ሌሎች የሰነዘራችሁት መጥፎ አስተያየት፣ ያስቀመጣችሁት ተገቢ ያልሆነ ፎቶግራፍ ወይም ስለ ግል ሕይወታችሁ ያሰፈራችሁት መረጃ ዘላቂ በሆነ መንገድ እንዲመዘገብና በማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚጠቀም ሁሉ በቀላሉ እንዲያገኘው ያደርጋል።” ይህ ማለት ደግሞ “በ15 ዓመታችሁ የፈጸማችሁትን ስህተት ከ10 ዓመት በኋላ ቀጣሪያችሁ ከኢንተርኔት ላይ ሊያገኘው ይችላል ማለት ነው” በማለት ራይት አክለው ተናግረዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ