የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 3/12 ገጽ 15-17
  • ተወዳጅ መሆን ስህተት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተወዳጅ መሆን ስህተት ነው?
  • ንቁ!—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ታዋቂ መሆን ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ጉልበተኞች ቢያስቸግሩኝ ምን ላድርግ?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ሌሎች ጓደኛቸው ሊያደርጉኝ ባይፈልጉ ምን ላድርግ?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ስለ እምነቴ ለሌሎች መናገር የሚያስፈራኝ ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2009
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 3/12 ገጽ 15-17

የወጣቶች ጥያቄ

ተወዳጅ መሆን ስህተት ነው?

ባዶ ቦታውን ሙላ።

ተወዳጅ መሆን ․․․․․

  1. ሀ. ሁልጊዜ ጥሩ ነው

  2. ለ. አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ነው

  3. ሐ. ፈጽሞ ጥሩ አይደለም

ትክክለኛው መልስ “ለ” ነው። ለምን? ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ መሆን ሲባል ተቀባይነት ማግኘት ማለት ነው፤ ይህ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ ስህተት አይደለም! መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች “የአሕዛብ ብርሃን” እንደሚሆኑና ሕዝቦች ወደ እነሱ እንደሚሳቡ ትንቢት ተናግሯል። (ኢሳይያስ 42:6፤ የሐዋርያት ሥራ 13:47) ከዚህ አንጻር ሲታይ ክርስቲያኖች ተወዳጅ ናቸው ማለት ይቻላል።

ይህን ታውቅ ነበር?

ኢየሱስ በሌሎች ዘንድ ተወዳጅ ነበር። ኢየሱስ ገና ታዳጊ ወጣት በነበረበት ጊዜም እንኳ “በአምላክና በሰው ፊት . . . ሞገስ” አግኝቶ ነበር። (ሉቃስ 2:52) ኢየሱስ ትልቅ ሰው በነበረበት ጊዜም “ከገሊላ፣ ከዲካፖሊስ፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ማዶ የመጡ እጅግ ብዙ ሰዎች [እንደተከተሉት]” መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።​—ማቴዎስ 4:25

ተወዳጅነት ማትረፉ ስህተት ነበር?

አልነበረም። ምክንያቱም ኢየሱስ ክብር ወይም ተወዳጅነት ለማትረፍ የሚፈልግ ሰው አይደለም፤ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘትም የተለየ ጥረት አላደረገም። ኢየሱስ ትክክል የሆነውን ከመፈጸም ውጪ ያደረገው ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ የሰዎችን ሞገስ ለማግኘት አስችሎታል። (ዮሐንስ 8:29, 30) በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሱስ፣ የሕዝቡ አቋም ተለዋዋጭ እንደሆነ ስለሚያውቅ በእነሱ ዘንድ ያተረፈው ተወዳጅነት ጊዜያዊ እንደሆነ ተገንዝቦ ነበር። እንዲያውም ይህ ሕዝብ ከጊዜ በኋላ እንደሚያስገድለው ተናግሯል!​—ሉቃስ 9:22

ዋናው ነጥብ፦

ተወዳጅነት ማትረፍ ሀብት እንደ ማግኘት ነው። ሀብት ማግኘት አብዛኛውን ጊዜ ስህተት አይደለም። ችግሩ ያለው ሰዎች ሀብት ለማግኘት ወይም ያገኙትን ሀብት ላለማጣት ሲሉ በሚወስዱት እርምጃ ላይ ነው።

ማስጠንቀቂያ!

ብዙ ወጣቶች ተወዳጅነት ለማትረፍ ሲሉ የማያደርጉት ነገር የለም። አንዳንዶቹ ሰው ያደረገውን የሚያደርጉ ልወደድ ባዮች ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ ሰዎችን በማስፈራራት ተቀባይነት ለማትረፍ የሚጥሩ ጉልበተኞች ናቸው።a

በቀጣዮቹ ገጾች ላይ ሰዎች ተወዳጅነት ለማትረፍ የሚከተሏቸውን እነዚህን ሁለት የተሳሳቱ ጎዳናዎች እንመለከታለን። ከዚያም የተሻለውን መንገድ እንመረምራለን።

www.watchtower.org/ype በሚለው ድረ ገጽ ላይ “Young People Ask” በሚለው ዓምድ ሥር ተጨማሪ ርዕሶችን በእንግሊዝኛ ማግኘት ይቻላል።

a መጽሐፍ ቅዱስ “ኔፊሊም” ስለሚባሉ “ከፍ ያለ ዝና ያተረፉ” ጉልበተኞች ይናገራል። እነዚህ ሰዎች ዋነኛ ፍላጎታቸው ክብር ማግኘት ነበር።​—ዘፍጥረት 6:4

ተወዳጅ ለመሆን የሚደረግ ጉዞ

ልወደድ ባዮች

  • በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት አለብኝ።

  • ተቀባይነት ለማግኘት ደግሞ እነሱን መምሰል አለብኝ።

“ከሁሉም ጋር ለመመሳሰል ስል ባሕርዬን ለመቀያየር ሞክሬ ነበር። መጀመሪያ ላይ የተሳካልኝ ይመስል ነበር። በኋላ ላይ ግን ተቀባይነት ለማግኘት ስል ፈጽሞ ማንነቴን መቀየር እንደሌለብኝ ተገነዘብኩ።”​—ኒኮል

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ብዙዎች ስላደረጉት ብቻ አንድን ነገር አታድርግ፤ . . . እነዚህ ሰዎች መጥፎ ነገር እንድታደርግ ቢያግባቡህ እሺ አትበል።”​—ዘፀአት 23:2 ሆሊ ባይብል​—ኢዚ ቱ ሪድ ቨርዥን

ጉልበተኞች

  • ብዙ ሰው እንደሚወደኝ አውቃለሁ፤ ደግሞም ነገሮች በዚህ መልኩ መቀጠል አለባቸው።

  • ያገኘሁትን ተቀባይነት ላለማጣት ማንኛውንም ነገር አደርጋለሁ፤ ሌሎችን መረማመጃ ማድረግ ቢኖርብኝም እንኳ ይህን ከማድረግ አልመለስም።

“ብዙ ልጆች ነገረኞች ናቸው፤ ጉልበተኛ የሆኑ ልጆች በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ስለሚያገኙ ዓይን አፋር የሆነ ልጅ እነሱ የተናገሩት ሁሉ ትክክል ይመስለዋል።”​—ራኬል

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ልክ ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ እንደምትፈልጉት ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው።”​—ሉቃስ 6:31

የተሻለው መንገድ

  1. የምትመራባቸውን መሥፈርቶች ለይተህ እወቅ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ጎልማሳ ሰዎች “ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር መለየት እንዲችሉ” ራሳቸውን እንደሚያሠለጥኑ ይናገራል።​—ዕብራውያን 5:14

    በስተግራ በኩል የሰፈሩትን ሦስት ነጥቦች በሥራ ላይ ስታውል በተወሰነ መጠን ተወዳጅነት ልታጣ ብትችልም ትክክለኛ አቋም ያላቸው ሰዎች ግን ይወዱሃል!

  2. ለምታምንበት ነገር አቋም ይኑርህ። የኢያሱ ዓይነት አቋም ይኑርህ፤ ኢያሱ “የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን” በማለት በልበ ሙሉነት ተናግሯል።​—ኢያሱ 24:15

  3. በመረጥከው መንገድ ተማመን። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ “አምላክ የኃይል . . . እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም” በማለት ጢሞቴዎስን አሳስቦታል።​—2 ጢሞቴዎስ 1:7

እኩዮችህ ምን ይላሉ?

Melissa

ሜሊሳ​—ትምህርት ቤት ውስጥ ያለ ማንኛውንም ልጅ መምሰል እንደምትችል የታወቀ ነው። ይሄ ግን በጣም ይደብራል! ክርስቲያን መሆንህ በምታደርገው መልካም ነገር ከሌሎች ለየት እንድትል ያደርግሃል። ይህ ሲባል ግን ከሰው የማትገጥም ትሆናለህ ማለት አይደለም። እንዲያውም ተወዳጅ ትሆናለህ።

Ashley

አሽሊ​—ተማሪዎቹ እንደማይወዱኝ ይሰማኝ ነበር፤ ወደ ክርስቲያናዊ ስብሰባ ስሄድ ግን በእኔነቴ የሚወዱኝን ጓደኞች አገኛለሁ። በዚህ ጊዜ በትምህርት ቤት ተወዳጅነት ለማትረፍ የነበረኝ ፍላጎት በንኖ ይጠፋል።

Phillip

ፊሊፕ​—በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ቁልፉ ለሰዎች በግለሰብ ደረጃ ትኩረት መስጠት ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለጓደኞቼ ጥቃቅን ነገሮችን ለማድረግ መጣር ጀምሬያለሁ፤ ይህ ደግሞ ከእነሱ ጋር ይበልጥ አቀራርቦኛል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ