የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g17 ቁጥር 4 ገጽ 9
  • ‘መልካም ስም ከብዙ ሀብት ይሻላል’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘መልካም ስም ከብዙ ሀብት ይሻላል’
  • ንቁ!—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትሕትና የድክመት ምልክት ነው ወይስ የጥንካሬ?
    ንቁ!—2007
  • ትሕትናን መልበስ ያለብን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • “ስምህ ይቀደስ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • እውነተኛ ትሕትና ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2017
g17 ቁጥር 4 ገጽ 9
መልካም ስም ያተረፈ አንድ መካኒክ

መልካም ስም ያለው ሰው የሌሎችን አክብሮትና አመኔታ ያተርፋል

‘መልካም ስም ከብዙ ሀብት ይሻላል’

መልካም ስም ትልቅ ዋጋ ያለው ነገር በመሆኑ በአንዳንድ አገሮች አንድ ሰው መጥፎ ወሬ በማስወራት፣ በጽሑፍ ወይም በመገናኛ ብዙኃን የሌላውን ስም ቢያጠፋ በሕግ ሊጠየቅ ይችላል። ይህ ደግሞ “መልካም ስም ከብዙ ሀብት ይመረጣል፤ መከበር ከብርና ከወርቅ ይሻላል” የሚለውን የጥንት አባባል ያስታውሰናል። (ምሳሌ 22:1) ይሁንና መልካም ስም ማትረፍ እንዲሁም የሌሎች ሰዎችን አክብሮት ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው? ይህን በተመለከተ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጠቃሚ ሐሳቦችን ማግኘት እንችላለን።

ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መዝሙር 15 ላይ ምን እንደሚል እንመልከት። መዝሙራዊው “[በአምላክ ድንኳን] ውስጥ በእንግድነት የሚስተናገድ ማን ነው?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ እንዲህ ብሏል፦ “ትክክል የሆነውን የሚያደርግ፣ በልቡም እውነትን የሚናገር ሰው ነው። . . . ስም አያጠፋም፤ በባልንጀራው ላይ መጥፎ ነገር አይሠራም፤ የወዳጆቹንም ስም አያጎድፍም። ነውረኛ የሆነን ሰው ሁሉ ይንቃል፤ . . . ጉዳት ላይ ሊጥለው ቢችልም እንኳ ቃሉን አያጥፍም። . . . ጉቦ አይቀበልም።” (መዝሙር 15:1-5) በእነዚህ ግሩም መሠረታዊ ሥርዓቶች የሚመራን ሰው ማክበር ቀላል ነው።

የሌሎችን አክብሮት ለማትረፍ የሚያስችለን ሌላው ባሕርይ ደግሞ ትሕትና ነው። ምሳሌ 15:33 “ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች” ይላል። ትሑት የሆኑ ሰዎች በምን ረገድ ማሻሻያ ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ይገነዘባሉ፤ ማሻሻያ ለማድረግም ይጥራሉ። በተጨማሪም አንድን ሰው ቅር አሰኝተው ከሆነ ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኞች ናቸው። (ያዕቆብ 3:2) ኩሩ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፤ ከዚህ ይልቅ በትንሽ በትልቁ ቅር ይሰኛሉ። ምሳሌ 16:18 “ኩራት ጥፋትን፣ የትዕቢት መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል” ይላል።

አንድ ሰው ስምህን ቢያጠፋስ? በቁጣ ገንፍለህ ወዲያው ምላሽ ትሰጣለህ? እንዲህ ብለህ ራስህን መጠየቅህ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፦ ‘ለራሴ ስም ለመሟገት የማደርገው ጥረት ወሬው ይበልጥ እንዲስፋፋ ያደርግ ይሆን?’ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ተገቢ የሚሆንባቸው ጊዜያት ሊኖሩ ቢችሉም “ከባልንጀራህ ጋር ስለ ራስህ ጉዳይ ተሟገት” እንጂ “ክስ ለመመሥረት አትቸኩል።” (ምሳሌ 25:8, 9)a ጉዳዩን በጥንቃቄና በሰከነ መንገድ ለመፍታት የምታደርገው ጥረት ለክስ ሂደት ወጪ ከማውጣትም ያድንሃል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሃይማኖት መጽሐፍ ብቻ አይደለም። አስተማማኝ የሕይወት መመሪያ የያዘ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ጥበብ የሚንጸባረቅበት ምክር ሥራ ላይ የሚያውሉ ሁሉ ግሩም ባሕርያትን ያዳብራሉ፤ ይህም መልካም ስምና አክብሮት እንዲያተርፉ ያስችላቸዋል።

a አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያስችሉ ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ማቴዎስ 5:23, 24 እና 18:15-17 ላይ ይገኛሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ