የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 1 ገጽ 14-15
  • ከውጥረት ነፃ የሆነ ሕይወት መምራት ትችላለህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከውጥረት ነፃ የሆነ ሕይወት መምራት ትችላለህ
  • ንቁ!—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2020
  • ውጥረትን መቆጣጠር የምንችልበት መንገድ
    ንቁ!—2010
  • በአምላክ መንግሥት ግዛት ውስጥ “ሰላም ይበዛል”
    ንቁ!—2019
  • ጥሩና መጥፎ ውጥረት
    ንቁ!—1998
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 1 ገጽ 14-15
አንድ ልጅ ከአባቱ ጋር ውኃ ውስጥ ሲጫወት፣ እናትየዋና ሴቶቹ ልጆች በባሕሩ ዳርቻ ሆነው ሲያዩ።

ከውጥረት እፎይታ ማግኘት

ከውጥረት ነፃ የሆነ ሕይወት መምራት ትችላለህ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ ያዘለ ምክር አላስፈላጊ ውጥረትን ለማስወገድ ይረዳናል። ሆኖም ውጥረት የሚፈጥሩ ነገሮችን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ እንደማንችል የታወቀ ነው። ፈጣሪያችን ግን ይችላል። በመሆኑም እኛን እንዲረዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስን ሾሞልናል። ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ሰው ሆኖ ምድር ላይ በኖረበት ወቅት ካከናወናቸው ነገሮች የሚበልጡ አስደናቂ ነገሮችን በቅርቡ በመላው ዓለም ያከናውናል። ለምሳሌ፦

ኢየሱስ ምድር ሳለ እንዳደረገው የታመሙትን ይፈውሳል።

“ሰዎችም በተለያየ በሽታና ከባድ ሕመም የሚሠቃዩትን . . . ሁሉ ወደ እሱ አመጡ፤ እሱም ፈወሳቸው።”—ማቴዎስ 4:24

ኢየሱስ ሁሉም ሰው መኖሪያ ቤትና በቂ ምግብ እንዲያገኝ ያደርጋል።

“[የክርስቶስ ተገዢዎች] ቤቶችን ይሠራሉ፤ በዚያም ይኖራሉ፤ ወይንንም ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። እነሱ በሠሩት ቤት ሌላ ሰው አይኖርም፤ እነሱ የተከሉትንም ሌላ ሰው አይበላውም።”—ኢሳይያስ 65:21, 22

የኢየሱስ አገዛዝ በመላው ዓለም ሰላምና ደህንነት ያሰፍናል።

“በእሱ ዘመን ጻድቅ ይለመልማል፤ ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ሰላም ይበዛል። ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ተገዢዎች ይኖሩታል። . . . ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።”—መዝሙር 72:7-9

ኢየሱስ የፍትሕ መጓደልን ያስወግዳል።

“ለችግረኛውና ለድሃው ያዝናል፤ የድሆችንም ሕይወት ያድናል። ከጭቆናና ከግፍ ይታደጋቸዋል።”—መዝሙር 72:13, 14

ኢየሱስ መከራን እና ሞትን ሳይቀር ያስወግዳል።

“ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”—ራእይ 21:4

“የሚያስጨንቅ ጊዜ”

“በአሁኑ ወቅት ዓለማችን ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በውጥረት፣ በጭንቀት፣ በሐዘንና በሥቃይ የተሞላ ሆኗል።”—መሐመድ ዩኒስ፣ የጋላፕ ማኔጂንግ ኤዲተር

ውጥረት ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ አሳማኝ መልስ ይሰጣል። ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 3:1 “በመጨረሻው ዘመን የሚያስጨንቅ ጊዜ እንደሚመጣ” ይናገራል። (አዲሱ መደበኛ ትርጉም) መጽሐፍ ቅዱስ ይህ የሆነው ሰዎች በሚኖራቸው መጥፎ ባሕርይ ምክንያት እንደሆነም ይገልጻል። ከእነዚህ መጥፎ ባሕርያት መካከል ስግብግብነት፣ ትዕቢት፣ ሃይማኖታዊ ግብዝነት፣ ዓመፅ፣ በቤተሰብ ውስጥ ፍቅር አለመኖር እንዲሁም ራስን አለመግዛት ይገኙበታል። (2 ጢሞቴዎስ 3:2-5) ኢየሱስ በሰማይ ያለው የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ ምድርን ሙሉ በሙሉ መግዛት ሲጀምር የመጨረሻው ዘመን ያበቃል።—ዳንኤል 2:44

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ