የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 4/1 ገጽ 30-31
  • ሙሴ ልዩ ኃላፊነት ተሰጠው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሙሴ ልዩ ኃላፊነት ተሰጠው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሰዶምና የገሞራ ጥፋት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ተአምራዊ ፈውሶችን አከናውኗል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ አድማጮቹን አስደነቀ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ፈተናን ተቋቁሟል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 4/1 ገጽ 30-31

ለታዳጊ ወጣቶች

ሙሴ ልዩ ኃላፊነት ተሰጠው

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው ሆነህ የሚከናወነውን ነገር እንደምትከታተል አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ይሖዋ አምላክና ሙሴ

ታሪኩ በአጭሩ፦ ሙሴ እስራኤላውያንን እየመራ ከግብፅ እንዲያወጣቸው ይሖዋ አዘዘው።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ዘፀአት 3:1-14⁠ን እና 4:1-17⁠ን አንብብ።

የሚነደው ቁጥቋጦ ምን ሊመስል እንደሚችል ግለጽ።

․․․․․

በ⁠ዘፀአት 3:4 ላይ እንደሚገኘው አምላክ ሙሴን ሲያናግረውና ሙሴ ምላሽ ሲሰጥ ፊቱ ላይ ምን ዓይነት ስሜት ይነበብ የነበረ ይመስልሃል? የድምፁ ቃናስ ምን ዓይነት ሊሆን ይችላል?

․․․․․

ሙሴ በ⁠ዘፀአት 3:11, 13 እና 4:1, 10 ላይ ተመዝግበው የሚገኙትን ጥያቄዎች ለይሖዋ ሲያቀርብ ምን ዓይነት ስሜት የነበረው ይመስልሃል?

․․․․․

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ምርምር ማድረግ የምትችልባቸውን መሣሪያዎች በመጠቀም “መሆን የምፈልገውን እሆናለሁ” የሚለው ሐረግ ምን ትርጉም እንዳለው ለማወቅ ሞክር። (ዘፀአት 3:14 NW) ሙሴ ስለ ይሖዋ ስም ጥያቄ ባነሳ ጊዜ ይሖዋ እንዲህ ያለ መልስ የሰጠው ለምን ይመስልሃል?a

․․․․․

ሙሴ በፈርዖን ፊት ለመቅረብ ያመነታው ለምን ይመስልሃል? (ፍንጭ፦ ዘኍልቍ 12:3⁠ን አንብብ።)

․․․․․

ሙሴ፣ ወገኖቹ በሆኑት እስራኤላውያን ፊት ለመቅረብ ያመነታውስ ለምን ሊሆን ይችላል?

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ሰዎች በራስ የመተማመን ስሜት ስለሚያጡበት ምክንያት

․․․․․

ይሖዋ በአንተና ባሉህ ችሎታዎች ላይ ስላለው እምነት

․․․․․

ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር፦

በራስ የመተማመን ስሜት የምታጣው በየትኞቹ የሕይወትህ ዘርፎች ነው?

․․․․․

የአቅም ገደብ ቢኖርብህም እንኳ ይሖዋ በየትኞቹ መንገዶች ሊጠቀምብህ ይችላል?

․․․․․

4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․

ይህን ዓምድ www.jw.org በተባለው ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a የይሖዋ ምሥክሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ወቅት ጥልቀት ያለው ምርምር እንድታደርግ ሊረዱህ የሚችሉ በርካታ መጻሕፍትንና ብሮሹሮችን አዘጋጅተዋል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በአካባቢህ ያሉትን የይሖዋ ምሥክሮች መጠየቅ ወይም ለዚህ መጽሔት አዘጋጆች መጻፍ ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ