የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 9/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትዳርን ዘላቂ የሚያደርገው ምንድን ነው?
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ትዳር ምን ይላል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ቤተሰብህ ደስተኛ መሆን የሚችለው እንዴት ነው?
    ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • ትዳራችሁን ታደጉ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ደስታ የሰፈነበት ትዳር መመሥረት የሚቻለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 9/1 ገጽ 16
[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ትዳርን አስደሳች ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ትዳርን አስደሳች ማድረግ ስለሚቻልበት መንገድ የሚሰጠው ምክር ጠቃሚ ነው፤ ምክንያቱም ይህን ምክር ያስጻፈው የጋብቻ መሥራች የሆነው ይሖዋ አምላክ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ትዳርን አስደሳች ለማደረግ የሚረዱ ባሕርያትን እንድናዳብር ያስተምረናል፤ ትዳርን ሊያናጉ የሚችሉ ዝንባሌዎችንም እንድናስወግድ ያስጠነቅቀናል። በተጨማሪም በትዳር ውስጥ ደስታ እንዲሰፍን በምን መንገድ የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ እንዳለብን ያስተምረናል።—ቆላስይስ 3:8-10, 12-14⁠ን አንብብ።

ባልና ሚስት እርስ በርስ መከባበር ይኖርባቸዋል። ሁለቱም፣ በትዳር ውስጥ የሚኖራቸውን ድርሻ በተመለከተ አምላክ የሰጠውን መመሪያ የሚጠብቁ ከሆነ ደስተኛ መሆን ይችላሉ።—ቆላስይስ 3:18, 19⁠ን አንብብ።

ትዳርን ዘላቂ የሚያደርገው ምንድን ነው?

የተጋቡ ሰዎች፣ ትዳራቸው ዘላቂ የሚሆነው እርስ በርስ የሚዋደዱ ከሆነ ነው። አምላክ፣ ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስተምረናል። እሱና ልጁ ኢየሱስ፣ የራስን ጥቅም መሥዋዕት በማድረግ ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ግሩም ምሳሌ ይሆኑናል።—1 ዮሐንስ 4:7, 8, 19⁠ን አንብብ።

ባልና ሚስት፣ ትዳርን የአምላክ ዝግጅት እንደሆነ አድርገው በመመልከት የሚያከብሩት ከሆነ ትዳራቸው ዘላቂ እንዲሆን ለማድረግ ይጥራሉ። አምላክ ጋብቻን ያቋቋመው በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ዘላቂ ጥምረት እንዲፈጠር በማሰብ ነው፤ ይህም ቤተሰቦች ጥበቃ እንዲያገኙና የደኅንነት ስሜት እንዲኖራቸው ያደርጋል። አምላክ ወንዶችንና ሴቶችን የፈጠረው አንዳቸው የሌላውን አካላዊ እና ስሜታዊ ፍላጎት ማሟላት እንዲችሉ አድርጎ መሆኑ ትዳር ዘላቂ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደርጋል። በተጨማሪም ሰዎችን የፈጠራቸው በራሱ መልክ ይኸውም እንደ እሱ፣ ፍቅር የማሳየት ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጎ ነው።—ዘፍጥረት 1:27⁠ን እና 2:18, 24⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 14 ተመልከት

www.jw.org/am ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማውረድ ይቻላል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ