የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 11/15 ገጽ 15
  • አምላክን ማገልገሉ መድኃኒት ሆነለት!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክን ማገልገሉ መድኃኒት ሆነለት!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 1,000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ልታደርጉት ትችላላችሁን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • አቅኚዎች በረከትን ይሰጣሉ፤ መልሰውም በረከት ያገኛሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ‘እንደ ሚዳቋ የምዘልበት’ ጊዜ ይመጣል
    ንቁ!—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 11/15 ገጽ 15
[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

አምላክን ማገልገሉ መድኃኒት ሆነለት!

በኬንያ ሁለት አቅኚዎች እያገለገሉ ሳለ አንድ ቤት አንኳኩ፤ ወደ ውስጥ ሲገቡ አንድ ትንሽ ሰው አልጋ ላይ ተኝቶ ነበር። ሰውነቱ ትንሽ፣ እጆቹም አጫጭር ስለነበሩ ወንድሞች በሁኔታው በጣም ተገረሙ። “አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል” የሚለውን አምላክ የሰጠውን ተስፋ ሲነግሩት ሰውየው ፊቱ በፈገግታ ተሞላ።—ኢሳ. 35:6

[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

አቅኚዎቹ፣ በአሁኑ ጊዜ በ30ዎቹ ዓመታት መገባደጃ ላይ የሚገኘው ኦኔስመስ የተባለው ይህ ሰው ኦስቲዎጄነሲስ ኢምፐርፌክታ የተሰኘ የአጥንት በሽታ እንዳለበት ተረዱ። አጥንቶቹ እጅግ ደካማ ከመሆናቸው የተነሳ በቀላሉ ሊሰበሩ ይችላሉ። ይህን በሽታ የሚፈውስ መድኃኒትም ሆነ ሕክምና ባለመኖሩ ኦኔስመስ ቀሪ ሕይወቱን በተሽከርካሪ ወንበር ላይ ሆኖ በሥቃይ እንደሚያሳልፍ ይሰማው ነበር።

ኦኔስመስ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና የቀረበለትን ግብዣ ተቀበለ። ይሁን እንጂ እናቱ ወደ ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች መሄዱ ለጉዳት ሊያጋልጠውና ተጨማሪ ሥቃይ ሊያስከትልበት ይችላል ብላ ስላሰበች ወደ ስብሰባ እንዲሄድ አልፈቀደችም። ስለዚህ ወንድሞች በስብሰባዎች ላይ የሚቀርበውን ትምህርት በመቅዳት ኦኔስመስ ቤቱ ሆኖ እንዲያዳምጥ ዝግጅት አደረጉለት። ለአምስት ወራት ካጠና በኋላ፣ ጉዳት ሊያስከትልበት ቢችልም እንኳ በስብሰባዎቹ ላይ ለመገኘት ወሰነ።

ታዲያ በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ መገኘቱ ሕመሙን አባባሰበት? በፍጹም። ኦኔስመስ “ስብሰባዎች ላይ በምገኝበት ጊዜ፣ የሚነዘንዘኝ ሥቃይ የቀነሰ ሆኖ ይሰማኛል” በማለት ተናግሯል። እንዲሻለው ያደረገው የተነገረው ተስፋ እንደሆነ ተሰምቶታል። የኦኔስመስ እናት የልጇ ስሜት መለወጡን ስትመለከት በጣም ተደስታ እሷም መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት ተስማማች። “የልጄ መድኃኒት አምላክን ማገልገል ነው” ትል ነበር።

ብዙም ሳይቆይ ኦኔስመስ ያልተጠመቀ አስፋፊ ሆነ። ከጊዜ በኋላ የተጠመቀ ሲሆን አሁን የጉባኤ አገልጋይ ሆኖ ያገለግላል። ኦኔስመስ እግሮቹንና አንድ እጁን መጠቀም ባይችልም በይሖዋ አገልግሎት አቅሙ የፈቀደለትን ሁሉ የማድረግ ፍላጎት ነበረው። ረዳት አቅኚ ለመሆን ቢፈልግም ቅጹን ለመሙላት አመንትቶ ነበር። ለምን? ያለ ሰው እርዳታ ተሽከርካሪ ወንበሩን ማንቀሳቀስ እንደማይችል ያውቅ ስለነበረ ነው። ይህን ጉዳይ ለእምነት አጋሮቹ በገለጸላቸው ጊዜ እንደሚረዱት ቃል ገቡለት። እነሱም ቃላቸውን በመጠበቅ ኦኔስመስ ረዳት አቅኚ እንዲሆን ረዱት።

ኦኔስመስ የዘወትር አቅኚ መሆን ቢፈልግም ያለ ሰው እርዳታ መንቀሳቀስ አለመቻሉ ያሳስበው ነበር። በአንድ ወቅት ግን የዕለት ጥቅስ ሲያነብ የሚያበረታታ ሐሳብ አገኘ። የዕለት ጥቅሱ መዝሙር 34:8 ሲሆን ይሖዋ “ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ” ይላል። ኦኔስመስ በዚህ ጥቅስ ላይ ካሰላሰለ በኋላ የዘወትር አቅኚ ለመሆን ወሰነ። በአሁኑ ጊዜ በሳምንት አራት ቀን የሚሰብክ ሲሆን ጥሩ መንፈሳዊ እድገት የሚያደርጉ በርከት ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች አሉት። በ2010 በአቅኚዎች አገልግሎት ትምህርት ቤት ተካፈለ። ኦኔስመስ መጀመሪያ ላይ ቤቱ መጥተው ከመሠከሩለት ወንድሞች አንዱ የትምህርት ቤቱ አስተማሪ መሆኑን ሲያውቅ በጣም ተደሰተ!

በአሁኑ ጊዜ ኦኔስመስ ወላጆቹን በሞት ያጣ ቢሆንም በጉባኤው ያሉት ወንድሞችና እህቶች በየዕለቱ የሚያስፈልገውን ነገር ያሟሉለታል። አሁን ላገኛቸው በረከቶች በሙሉ አመስጋኝ ሲሆን “ታምሜአለሁ” የሚል የማይኖርበትን ጊዜ በጉጉት ይጠብቃል።—ኢሳ. 33:24

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ