መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
አምላክ ለሁሉም ጸሎቶች መልስ ይሰጣል?
የእነማንን ጸሎት የሚመልስ ይመስልሃል?
የሁሉንም ሰዎች
የአንዳንድ ሰዎችን
የማንንም አይመልስም
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
“ይሖዋ . . . በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።”—መዝሙር 145:18
መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?
አምላክ በእሱ ላይ የሚያምፁ ሰዎችን ጸሎት አይሰማም። (ኢሳይያስ 1:15) ሆኖም መንገዳቸውን በማስተካከል ከአምላክ ጋር ያላቸውን ዝምድና ያበላሸባቸውን ‘ችግር መፍታት’ ይችላሉ።—ኢሳይያስ 1:18
አምላክ መልስ የሚሰጠው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት መሥፈርቶች ጋር ለሚስማሙ ጸሎቶች ነው።—1 ዮሐንስ 5:14
መጸለይ ያለብን እንዴት ሆነን ነው?
ሰዎች ምን ብለው ያምናሉ? አንዳንድ ሰዎች በሚጸልዩበት ጊዜ ሁሉ መንበርከክ፣ ማጎንበስ ወይም እጃቸውን ማጋጠም እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። አንተ ምን ይመስልሃል?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
አምላክ የተለያዩ ሰዎች ‘ተቀምጠው’ ወይም “ተነስተው፣” አሊያም ‘ተደፍተው’ ወይም ‘ተንበርክከው’ ያቀረቡትን ጸሎት ሰምቷል። (1 ዜና መዋዕል 17:16፤ 2 ዜና መዋዕል 30:27፤ ዕዝራ 10:1፤ የሐዋርያት ሥራ 9:40) በመሆኑም እንዴትም ሆነን ብንጸልይ ለአምላክ ለውጥ አያመጣም።
መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?
አምላክ ትሑት የሆኑ ሰዎችን ጸሎት ይሰማል።—መዝሙር 138:6
በማንኛውም ቋንቋ ሌላው ቀርቶ ድምፅ ሳታወጣም መጸለይ ትችላለህ።—2 ዜና መዋዕል 6:32, 33፤ ነህምያ 2:1-6