የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp22 ቁጥር 1 ገጽ 12-13
  • 4 | በአምላክ እርዳታ ጥላቻን ድል አድርግ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 4 | በአምላክ እርዳታ ጥላቻን ድል አድርግ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦
  • ምን ማለት ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የሚቻለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
  • ጥላቻን ድል ማድረግ እንችላለን!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
  • ጥላቻ የተስፋፋው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
wp22 ቁጥር 1 ገጽ 12-13
ሰዎች ወደተገለጠ ትልቅ መጽሐፍ ቅዱስ እየሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱሱ እያበራባቸው ነው። የሰዎቹ ጥላ ቀደም ሲል የነበራቸውን ጥላቻ ያሳያል።

የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የሚቻለው እንዴት ነው?

4 | በአምላክ እርዳታ ጥላቻን ድል አድርግ

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦

“የመንፈስ ፍሬ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ደግነት፣ ጥሩነት፣ እምነት፣ ገርነት፣ ራስን መግዛት ነው።”—ገላትያ 5:22, 23

ምን ማለት ነው?

በአምላክ እርዳታ የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ እንችላለን። የአምላክ ቅዱስ መንፈስ በራሳችን ልናዳብር የማንችላቸውን ግሩም ባሕርያት እንድናፈራ ያስችለናል። ስለዚህ በራሳችን ኃይል ጥላቻን ለማሸነፍ ከመሞከር ይልቅ በአምላክ እርዳታ መታመናችን የተሻለ ነው። እንዲህ ካደረግን የሐዋርያው ጳውሎስ ዓይነት ስሜት ይኖረናል፤ ጳውሎስ “ኃይልን በሚሰጠኝ በእሱ አማካኝነት ለሁሉም ነገር የሚሆን ብርታት አለኝ” በማለት ጽፏል። (ፊልጵስዩስ 4:13) በእርግጥም “እኔን የሚረዳኝ . . . ይሖዋ ነው” ማለት እንችላለን።—መዝሙር 121:2

ምን ማድረግ ትችላለህ?

“ግልፍተኛ የነበርኩት ሰው ተለውጬ ሰላማዊ እንድሆን ይሖዋ ረድቶኛል።”—ዎልዶ

ይሖዋ መንፈስ ቅዱስን እንዲሰጥህ ከልብህ ጸልይ። (ሉቃስ 11:13) ግሩም ባሕርያትን ለማዳበር እንዲረዳህ ጠይቀው። መጽሐፍ ቅዱስ ጥላቻን ለማሸነፍ ስለሚረዱ ባሕርያት ምን እንደሚል አጥና፤ ከእነዚህ ባሕርያት መካከል ፍቅር፣ ሰላም፣ ትዕግሥትና ራስን መግዛት ይገኙበታል። እነዚህን ባሕርያት ማንጸባረቅ የምትችልባቸውን አጋጣሚዎች ፈልግ። በተጨማሪም እነዚህን ባሕርያት ለማዳበር ጥረት ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ጊዜ አሳልፍ። እንዲህ ያሉ ሰዎች “ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች” እንድትነቃቃ ይረዱሃል።—ዕብራውያን 10:24

እውነተኛ ታሪክ—ዎልዶ

ዓመፅንና ጥላቻን ድል አድርጓል

ዎልዶ።

ዎልዶ በልጅነቱ ብዙ መከራ ስለደረሰበት ያደገው በጥላቻ ተሞልቶ ነው። እንዲህ ብሏል፦ “ከዕፅ አዘዋዋሪዎች ጋር በጎዳና ላይ በሚደረጉ ግጭቶች ብዙ ጊዜ እካፈል የነበረ ሲሆን . . . በአንድ ወቅት የእኛ ተቀናቃኝ የሆነ አንድ የወንበዴዎች ቡድን እኔን ለማስገደል በጭካኔው የታወቀ ነፍሰ ገዳይ ቀጠረ፤ ሰውየው በስለት ቢወጋኝም ሳልሞት ማምለጥ ቻልኩ።”

ዎልዶ ባለቤቱ መጽሐፍ ቅዱስን ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ማጥናት ስትጀምር አልተደሰተም ነበር። እንዲህ ብሏል፦ “የይሖዋ ምሥክሮችን እጠላቸው ስለነበር ብዙ ጊዜ መጥፎ ስድብ ሰድቤያቸዋለሁ። እነሱ ግን ምንጊዜም በሰላማዊ መንገድ ያናግሩኝ ነበር።”

ውሎ አድሮ ዎልዶም መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀመረ። ዎልዶ “የምማረውን ነገር በሥራ ላይ ማዋል ቀላል አልነበረም። የግልፍተኝነት ጠባዬን መቆጣጠር ፈጽሞ እንደማይሳካልኝ ተሰምቶኝ ነበር” ብሏል። ሆኖም ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኘው አንድ ትምህርት በሕይወቱ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል።

ዎልዶ እንዲህ ብሏል፦ “መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስጠናኝ አሌሃንድሮ፣ አንድ ቀን ገላትያ 5:22, 23⁠ን እንዳነብብ ጠየቀኝ። . . . አሌሃንድሮ እነዚህን ባሕርያት ማዳበር የምችለው በራሴ ጥንካሬ ሳይሆን በአምላክ ቅዱስ መንፈስ እርዳታ እንደሆነ ገለጸልኝ። ይህ እውነት አመለካከቴን ሙሉ በሙሉ ለወጠው!”

ዎልዶ በአምላክ እርዳታ በመታመን የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ ችሏል። እንዲህ ብሏል፦ “ዘመዶቼና የቀድሞ ጓደኞቼ ያደረግሁትን ለውጥ ማመን ያቅታቸዋል።” አክሎም “ግልፍተኛ የነበርኩት ሰው ተለውጬ ሰላማዊ እንድሆን ይሖዋ ረድቶኛል” ብሏል።

የዎልዶ ታሪክ በጥቅምት 1, 2013 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 12-13 ላይ ወጥቷል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ