የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 26
  • አምላክ ወደ እሱ ብጸልይ ይረዳኛል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ወደ እሱ ብጸልይ ይረዳኛል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • በእርግጥ ይሖዋ ይሰማናል?
    አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • አምላክ ጸሎታችንን ይሰማል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር መቀራረብ
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 26

አምላክ ወደ እሱ ብጸልይ ይረዳኛል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አዎ፣ አምላክ ከፈቃዱ ጋር የሚስማሙ ነገሮችን ከልባቸው የሚጠይቁ ሰዎችን ይረዳቸዋል። ከዚህ ቀደም ጸልየህ ባታውቅም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‘አምላክ ሆይ፣ እርዳኝ’ ብለው የጸለዩ ሰዎችን ታሪክ ማንበብህ ሊያጽናናህ ይችላል። ለምሳሌ ያህል፦

  • “እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ርዳኝ፤ እንደ ምሕረትህም አድነኝ።”—መዝሙር 109:26

  • “እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማ፤ ማረኝም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ረዳት ሁነኝ።”—መዝሙር 30:10

እርግጥ ነው፣ እነዚህን ሐሳቦች የጻፈው ግለሰብ በአምላክ ላይ ጠንካራ እምነት እንደነበረው ግልጽ ነው። ያም ሆኖ አምላክ ‘ልባቸውና መንፈሳቸው የተሰበረ’ ሰዎች በሙሉ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ይዘው ወደ እሱ የሚቀርቡትን ጸሎት ይሰማል።​—መዝሙር 34:18

አምላክ ሩቅ እንደሆነ ወይም የአንተ ችግር እንደማያሳስበው ተሰምቶህ ስጋት ሊያድርብህ አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያላል፦ “እግዚአብሔር በከፍታ ስፍራ ቢሆንም፣ ዝቅ ያለውን ይመለከተዋል፤ ትዕቢተኛውን ከሩቅ ያውቀዋል።” (መዝሙር 138:6) እንዲያውም ኢየሱስ በአንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱን “የራሳችሁ ፀጉር እንኳ አንድ ሳይቀር ተቆጥሯል” ብሏቸው ነበር። (ማቴዎስ 10:30) አምላክ ስለ ራሳችን የማናውቃቸውን ጥቃቅን ነገሮች እንኳ ያውቃል። ታዲያ ስለሚያስጨንቀን ነገር ስንጸልይ እኛን ለማዳመጥ ይበልጥ ፈቃደኛ ይሆናል ብሉ ማሰቡ ምክንያታዊ አይሆንም?​—1 ጴጥሮስ 5:7

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ