የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 64
  • ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀም ይኖርብናል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀም ይኖርብናል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • አምላክን በምስሎች ተጠቅመን ማምለክ ይኖርብናል?
    ንቁ!—2008
  • የይሖዋ ምሥክሮች ምስሎችን ለአምልኮ የማይጠቀሙት ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ምስሎች
    ንቁ!—2014
  • ምስሎች ወደ አምላክ ሊያቀርቡህ ይችላሉን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 64

ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀም ይኖርብናል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

በፍጹም አይኖርብንም። አምላክ ለጥንቶቹ እስራኤላውያን የሰጣቸውን ሕጎች አስመልክቶ ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒዲያ እንዲህ ብሏል፦ “ከተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ማየት እንደሚቻለው ምስሎች በእውነተኛው አምልኮ ውስጥ ቦታ የላቸውም።” የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንደ ምሳሌ እንውሰድ፦

  • “በላይ በሰማይ ወይም በታች በምድር ካለው ወይም በውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ነገሮች በማናቸውም ምስል ለራስህ ጣዖትን አታብጅ። አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ . . . ቀናተኛ አምላክ ነኝ።” (ዘፀአት 20:4, 5) አምላክ “ቀናተኛ” ወይም እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ ስለሆነ ምስሎችን፣ ሥዕሎችን፣ ጣዖቶችን፣ ሐውልቶችን ወይም ምልክቶችን ለአምልኮ እንድንጠቀም አይፈልግም።

  • “ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።” (ኢሳይያስ 42:8 የ1954 ትርጉም) አምላክ፣ በምስሎች አማካኝነት የሚቀርብን አምልኮ ያወግዛል። አንዳንድ እስራኤላውያን የጥጃ ምስል ተጠቅመው ለእሱ አምልኮ ለማቅረብ በሞከሩበት ወቅት አምላክ “[ሕዝቡ] ኃጢአት ሠርተዋል” በማለት ተናግሯል።​—ዘፀአት 32:7-9 የ1954 ትርጉም

  • “አምላክ በሰው ጥበብና የፈጠራ ችሎታ ከወርቅ ወይም ከብር ወይም ከድንጋይ የተቀረጸን ነገር ይመስላል ብለን ልናስብ አይገባም።” (የሐዋርያት ሥራ 17:29) “በሰው ጥበብና የፈጠራ ችሎታ” የተቀረጹ ምስሎችን ተጠቅመው አምልኮ ከሚያቀርቡ ሰዎች በተለየ መልኩ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ክርስቲያኖች የሚመላለሱት “በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።”​—2 ቆሮንቶስ 5:7

  • “ራሳችሁን ከጣዖቶች ጠብቁ።” (1 ዮሐንስ 5:21) ለእስራኤላውያንም ሆነ ለክርስቲያኖች የተሰጡት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ትእዛዛት እንደሚያሳዩት አምላክ ሥዕሎችን ወይም ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀምን ያወግዛል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ