ምሳሌ
9 እውነተኛ ጥበብ ቤቷን ሠራች፤
ሰባቱን ምሰሶዎቿንም ጠርባ አዘጋጀች።
3 ከከተማዋ በላይ ባሉ ከፍታ ቦታዎች ላይ ሆነው
እንዲህ ብለው እንዲጣሩ ሴት አገልጋዮቿን ላከች፦+
4 “ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።”
ማስተዋል* ለጎደለው እንዲህ ትላለች፦
5 “ኑ፣ ያዘጋጀሁትን ምግብ ብሉ፤
የደባለቅኩትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።
7 ፌዘኛን የሚያርም በራሱ ላይ ውርደት ያመጣል፤+
ክፉን ሰው የሚወቅስም ሁሉ ጉዳት ይደርስበታል።
8 ፌዘኛን አትውቀስ፤ አለዚያ ይጠላሃል።+
ጥበበኛን ሰው ውቀሰው፤ እሱም ይወድሃል።+
9 ጥበበኛን ሰው አስተምረው፤ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል።+
ጻድቅን ሰው አስተምረው፤ ተጨማሪ እውቀት ያገኛል።
11 በእኔ ምክንያት ዘመንህ ይረዝማል፤+
በሕይወትህም ላይ ዕድሜ ይጨመርልሃል።
12 ጥበበኛ ብትሆን፣ ጥበበኛነትህ የሚጠቅመው ራስህን ነው፤
ፌዘኛ ብትሆን ግን መዘዙን የምትቀበለው አንተው ነህ።
13 ማስተዋል የጎደላት ሴት ጯኺ ናት።+
እሷ ጨርሶ ማመዛዘን አትችልም፤ ደግሞም አንዳች ነገር አታውቅም።
16 “ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።”
17 “የተሰረቀ ውኃ ይጣፍጣል፤
ተደብቀው የበሉት ምግብም ይጥማል።”+